





ህብረ ብሔራዊ የእህትማማችነት እሴትን በማዳበር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መትጋት ይጠበቃል ሲሉ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ ገለጹ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሴቶች ፌደሬሽን አንደኛ መደበኛ ጉባኤ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው
በጉባኤው የ2017 የእስካሁን ሥራዎች ሪፖርት መገምገም፣ አመራሮችን መልሶ ማደራጀት፣በፌደራል የሴቶች ፌድሬሽን ሶስተኛ መበደኛ ጉባኤ ክልሉን ወክለው የሚሳተፉ አባላትን የተጓደለ በማሟላት እወቅና መስጠት ፣የፌድሬሽኑን አደረጃጀቶች ለማጠናከር ስልጠናዎች ይስጣል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፌድሬሽኑ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
ሴቶችን በማህበራዊ ልማትና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በተናበበና በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የዲሞክራሲ እሴቶችን በማዳበር ሴቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ እያተደረጉት ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሪት ለምለም አምሳሉ በበኩላቸው ቢሮው የተለያዩ አደረጃጀቶችንና የአሰራር ስርዓቶችን በማጠናከር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተልዕኮውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ፌደሬሽኑ እስካሁን ባለው በተቀናጀ ጥረት እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን አጠናከሮ በማስቀጠል በድክመት የታዩትን ጉዳዮች ፈጥኖ በማረም ጠንካራ ፌድሬሽን ሊኖር እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
የክልሉ የሴቶች ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ትዕግስት ወርቁ በፌደሬሽኑ እስካሁን እየተከናወኑ ያሉትን ሥራዎች ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛል።
