




በምዕራብ ኦሞ ዞን “ትዉልድ በመምህር ይቀርጻል ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል “በሚል መሪ ሃሳብ ዞናዊ የትምህርት ማህበረሰብ ዉይይት እየተደረገ ይገኛል።
በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ እንደተናገሩት ለሀገራችን ብልጽግና ስኬት የመምህራን ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የሁሉም ሙያዎች መሰረት ትምህርት መሆኑ የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው መምህራን ሙያቸውን በአግባቡ በመያዝ ብቁ ዜጋ የማፍራት ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የዞኑ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበቃ ፈለቀ በበኩላቸው ትዉልድ በመምህራን እንደሚቀርጽ ጠቅሰው ትዉልድ በአግባቡ ከተቀረፀ ሀገር ትበለጽጋለች ብልዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
