በተጠናቀቀው በ2015 በጀት ዓመት ከ44 ሺህ በላይ ኩነቶች መመዝገባቸው ተገለፀ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ የ2015 ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በምክክር መድረኩ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኩሪያ በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት 48 ሺህ 588 ኩነቶችን ለመመዝገብ ታቅዶ 44 ሺህ 213 ኩነቶች ሊመዘገብ መቻሉን አብራርተዋል።

ምዝገባው በአምስት የኩነት ዓይነቶች ማለትም በልደት፣ ሞት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ጉድፈቻ የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 91% እንደሆነም ኃላፊው ገልጸዋል።

ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎች የሚያበረክተው ጠቀሜታ ባሻገርም ዜጎች ከመንግሰት ማግኘት የሚገባቸውንና መንግስት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎቶችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ዕቅድን መሠረት አድርገው ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያገለግልም አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል።

አክለውም ዜጎች ከሀገር አልፎ የውጭ የስራ ዕድል እንዲያገኙም የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እጅግ ወሳኝ እንደሆነም አስረድተዋል።

በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት የተሰሩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ጉድለቶችን በማረም በ2016 በጀት ዓመት በ5ቱም ኩነት አይነቶች 61 ሺህ 56 ኩነቶችን ለመመዝገብ ግብ ተጥሎ ወደ ስራ መገባቱንም አቶ ተስፋዬ አስታውቀዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *