
የደን ሀብት ዲጂታል መረጃ የማደራጀት እና ለውሳኔ እንዲያገለግሉ መረጃዎች የሚደራጁበት የጥናትና ምርምር መርሃ ግብር የፕሮጀክት ግምገማ ተጠናቋል ።
ክልላዊ የደን ሀብት መረጃን ወደ ድጂታል በመቀየር ሚዛናዊ የሆነ የደን ሀብት ሊያሳይ የሚችል መረጃ ማደራጀት ይገባልም ተብሏል።
በዚህ ግምገማ የተገኙ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በክልሉ ህብረተሰቡ ለደን የሰጠው ዋጋ በውል ባለመታወቁ ተጠቃሚ መሆን እንዳልቻሉ ተናግረዋል ።
የተጠናው ፕሮጀክት እውን ሲሆን ለህዝቡ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል።
ደንን የመጠበቅ የመንከባከብ እና የማልማት ጉዳይ ለነገ የሚባል ተግባር ባለመሆኑ እስከ ታችኛው እርከን ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባልም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የክልሉ ህዝብ ከደን ጋር ያለው ቁርኝት ከፍተኛ በመሆኑ የቀደሙት አባቶች በደን ላይ ያሏቸውን አቋም የአሁኑ ትውልድ ሊደግመው ይገባልም ብለዋል በአስተያየታቸው ።
የክልሉ ህዝብ ከደን ጋር ያለው ቁርኝት የተነጣጠለ ባለመሆኑ የቀደሙት አባቶች በደን ላይ ያሏቸውን አቋም የአሁኑ ትውልድ ሊደግመው ይገባልም ብለዋል በአስተያየታቸው ።
የክልሉ ደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን የክልሉ መንግስት ልዩ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል ።

ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት በዕውቀት የሚመራ በመሆኑ ከሁሉም ዞኖች የበቃ የሰው ሀይል ለመረጃ መሰብሰብ የሚያስፈልግ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በስትሪንግ ኮሚቴ እየተመራ እንደሚከናወን አብራርተዋል ።

ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆንም ለማህበረሰቡ መረጃዎችን ለመስጠት እንዲያስችልም በሚዲያ የሚሰራጭ የተለያዩ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸውንም እንዲሁ ገልጸዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን መንግስታዊ የሆኑና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸውም ገልጸዋል ።

ይህ ፕሮጀክት ዉጤታማ እንዲሆን ተገቢዉ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
በታጠቅ አበበ
