

በመድረኩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ እንደተናገሩት ዛሬ የሚንመሰርተው ክልል አቀፍ ገለልተኛ የወንጀል መከላከል አማካሪ ምክር ቤት ወንጀልን በተደረጀና በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል ትልቅ አቅም አለው ብለዋል፡፡
በክልሉ ገለልተኛ የአማካሪ ምክር ቤት መመስረት ያሰፈለገበት ዋና ምክንያት ወንጀል የመከላከሉ ስራ ሁላንታናዊ የዜጎች ተሳትፎ ስለሚያስፈልግና አንዱ የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበት በመሆኑ ነው
ብለዋል።
ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ከፖሊስ እና ከማህበረሰቡ የተወጣጡ አባላት ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ እንቅሰቃሴ ላይ ያለውን ነገር እየለየ፣ ምክረ ሀሳብ እየሰጠ እና የራሱን ኃላፊነት በማህበረሰቡ ውስጥ እየተወጣ የሚቀጥል እንደሆነም ኮሚሽነር ሰብስቤ ገልጸዋል፡፡
የክልሉ ሠላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ሠላም ለሁሉም ወሳኝ መሆኑን ገልጸው ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት በየአካባቢው የሚፈጠሩ ግጭቶች መንስኤ በማጥናት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አንፃራዊ ሠላም እንዲመጣ ተኪ የሌለው ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል።
የመድረክ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ውስብስብ የሆነ የወንጀል ድርጊቶች እየተፈፀሙ መሆኑን ጠቅሰው ክልሉን ከወንጀል ነፃ ለማድረግ በተሰጣቸው ኃላፊነት መሠረት ከፖሊስ ጋር ተቀናጅተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
መድረኩ ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖን የክልሉ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ ብርሃኑ ኃይሌን ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ በመምረጥና ቃለመሃላ በመፈፀም ተጠናቋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
