




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የክልልና የዞን ምክር ቤቶች 6ኛ ዙር የጋራ ምክክር መድረክ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ መካሄድ ጀምሯል ።
መድረኩ በኮንታ ዞን ምክር ቤት አዘጋጅነትና በክልል ምክር ቤት አስተባባሪነት የሚካሄድ እንደሆነ ተገልጿል ።
በምክክር መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፌ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቶች በህገመንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በየደረጃው የሚገኙ አሰፈጻሚ አካላት ላይ ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የድጋፍ ስራዎች አዎንታዊ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል ።
ይሁን እንጂ በየደረጃው በሁሉም ቦታ ወጥ የሆነ አሠራር ከማምጣት አንጻር የሚታዩ ክፍተቶችን ለማረምና ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር በየደረጃው የሚታየውን ልዩነት ለማጥበብ መድረኩ ከፍተኛ ሚና መኖሩን አፌ ጉባኤው ተናግረዋል ።
አክለውም የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክ የተሻለ ልምድን በመቅሰ፣ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማረምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በመመካከር በየአካባቢው ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በመጨረሻም የኮንታ ዞን በገባው ቃል መሠረት ደማቅ ዝግጅት በማድረግ እንግዳን በመቀበሉ ምስጋና አቀርበዋል።
ምክክር መድረኩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ዞኑ የውስጥ ገቢ አቅምን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በዘለቂነት ለመፍታት በርካታተግባራትን ከማከናወኑም ባሻገር ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን አንስተዋል ።
በመሆኑም ከመድረኩ ጎን ለጎን በዞኑ የተሰሩ የተለያዩ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በመጎብኘት ልምድ የሚቀሰምበት እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል ።
እንግዶች የእንኳን ደህና መልዕክት ያስተላለፉት የኮንታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ብርሃኑ አቱሞ የመድረኩ ፋይዳው በየደረጃው የሚታዩ ክፍቶችን ለማረምና ባጋጠሙ ችግሮች ላይ በመወያየት ለመፍታትና ውሳኔ ለማስተላለፍ እንደሚያግዝ አንስተዋል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎች የ5ኛ ዙር የምክክር መድረክ ረቂቅ ቃለ ጉባኤውን በመጽደቅ በዞኑ አመያ ከተማ አስተዳደር ጨታ ቀጭ ቀጫ ቀበሌ በሞዴል አርሶ አደሮች የተሰሩ የልማት ሥራዎች ጉብኝት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
በጌታሁን ግርማ
