ሚዲያው ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ በይዘት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የድህረ-ገጽና ማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በታርጫ ከተማ ተከናውኗል።

በመርሀ-ግብሩ ተገኝተው የሚዲያ ኔትወርክ ስራውን በይፋ ያስጀመሩት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የሚዲያ ኔትወርኩ ሥራ-አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፥ አቶ ፍቅሬ አማን ሚዲያው ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲወጣ በይዘት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ጥራት፣ ተዓማኒነት ሚዛናዊነት የሚዲያ ኔትወርኩ ተቀዳሚ መገለጫ መሆን እንዳለበት የገለጹት አቶ ፍቅሬ ሚዲያውን ህዝባዊነት በማረጋገጥ ተደራሽነትን ማስፋት አለበት ብለዋል።

ሚዲያው አለም የደረሰበትን የአስተሳሰብና የመረጃ ፍስት ደረጃ በውል በመገንዘብ የቀዳሚነት ሚናው መውጣት አለበት ያሉት አቶ ፍቅሬ አፍራሽ ሀሳቦች በመመከት ለህዝቦች አንድነት መጠናከር መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሚዲያ ኔትወርኩ በተሟላ መልኩ ተግባሩን እንዲከወን የተቋማት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በአጽንኦት ተናግረዋል።

ለሚዲያ ተቋም ተወዳዳሪነት ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የጠየቁት የሚዲያ ኔትወርኩ ስራ-አስኪያጅ አቶ መንግሥቱ መኩሪያ የክልሉን ህዝብ ሠላም ልማት እንዲሁም ሁለንተናዊ ለውጦች ያለውን አበርክተው በትጋት መውጣት አለብን ብለዋል።

ለሚዲያው ችግር ፈቺ ድጋፍ በማድረግ ማደራጀት እንደሚገባ የገለጹት የመድረኩ ተሳታፊዎች በቁርጠኝነት ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመርሀ-ግብሩ የተገኙ ታዳሚዎች የሚዲያ ኔትወርክ፣ የከተማዊን የኮሪደር ልማትና የሌማት ትሩፋት የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *