ክልላዊ ማጠቃለያ የመምህራን ውይይት እየተካሄደ ነዉ

Spread the love

“ትውልድ በመምህራን ይቀረጻል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል የሚካሄደው ክልላዊ ማጠቃለያ የመምህራን ውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ከክልሉ ከሁሉም አከባቢ ትምህርት ቤቶች ከተወጣጡ የትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራን ጋር የሚደረገዉ የውይይት መድረክ በየደረጃው ሲካሄድ ቆይተዉ በዛሬው ቀን ማጠቃለያ እየተደረገ ይገኛል።

መምህራን ትውልድን በመቅረጽና ሀገርን በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና አይተኬ ነዉ።

በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘዉዴን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እና ከክልሉ ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ የትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራኞች ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *