በክልሉ የተጀመሩ የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልክ እንዲከናወኑ ለማስቻል ኮሚሽኑ የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተገለፀ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ስር የRCFSP ፕሮጀክት በተገኘ ድጋፍ ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ 6 ዞኖችና 6 ወረዳዎች ለተውጣጡ የስነ-ምግባር ኦፊሴሮች በሙስና መከላከል ዙሪያ የተዘጋጀ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳግም ዳንኤል፣እንዳሉት ሙስናና ብልሹ አሰራር የሀገራችንም ሆነ የክልላችንን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት የሚገታ ፣የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ጥረታችንን የሚያደናቅፍ መሆኑንና በመገንዘብ የተጀመረውን የፀረሙስና ትግሉን በማጠናከር በርካታ እርምጃዎችን በመዉሰድ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደረግላቸው የተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ከሙስናና ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልክ እንዲከናወን ለማስቻል ኮሚሽኑ የመከታተል እና የማረጋገጥ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት የ/RCFSP/የገጠር ትስስር ምግብ ዋስትና ድጋፍ ፕሮጀክት አፈፃፀምን ከሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መዘጋጀቱንም ምክትል ኮሚሽነር ዳግም ዳንኤል ገልጸዋል።

በመድረኩም በክልሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በመንገድ ትራንስፖርት ልማት ቢሮ ስር የRCFSP ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረግባቸው ከ6ዞኖችና ከ6ወረዳዎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *