ውስን የኾነውን የመንግሥት በጀት ለህዝብ ልማት ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም እንደሚገባ ተመላከተ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የ2018 በጀት አመት፤ የበጀት ሰሚ መርሀ-ግብር በቦንጋ ከተማ መካሄድ ተጀመሯል።

በበጀት ስሚ መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ እንደገለጹት፥ ውስን የኾነውን የመንግሥት በጀት ለህዝብ ልማት ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ባለበጀት ተቋማት የ2018 ዓመት በጀታቸውን ሲያዘጋጁ የተሰጣቸውን የበጀት ጣሪያ ባገናዘበ መልኩ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው ነው ወ/ሮ ወሰነች የገለጹት።

ተቋማት በበጀት ግምገማው የሚሰጣቸውን ዝርዝር አስተያየቶች በግብዓትነት በመጠቀም የበጀት ጣራን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እቅዳቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከልሰው ለፋይናንስ ቢሮ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸውም ወ/ሮ ወሰነች የገለጹት።

ወ/ሮ ወሰነች አክለው መስሪያ ቤቶች ለዋና ዋና የልማት ፕረጀክቶች ማስፈፀሚያ ትኩረት በመስጠት የወጪ ቁጠባን መሰረት ያደረገ የእቅድ አፈጻጸም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቻው ገልጸው እስከ ሰኔ አጋማሽ ባለው ጊዜ ሁሉም ባለበጀት ተቋማት የበጀት ሰሚ መርሀ-ግብር በየክላስተሩ እንደሚያከናውን ተናግረዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የፊሲካል ፖሊሲና

የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ኡሮ በበኩላቸው፥ የሚመደበው በጀት ውስን በመሆኑ የህዝብ ተጠቃሚነት ለሚያሳድጉ ዋና ዋና የልማት መስኮችን ትኩረት ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በጀቱ የክልሉ መንግሥት የልማትና መልካም አስተዳደር ማስፈፀሚያ መሆኑን የጠቆሙት አቶ መለሰ ተቋማት የውስጥ አደረጃጀት በመፈተሽ እና አሰራሮችን በማዘመን የበጀት ውጤታማነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የዘንድሮው በጀት ዓመት የበጀት ሰሚ ከወትሮ በተለየ የክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር በቅንጅት የሚገመገም በመሆኑ የእቅድ አፈጻጸም ለመከታተል እና የበጀት አጠቃቀም ውጤታማነት ከተግባር አፈጻጸም ጋር ለመመዘን ምቹ ሁኔታ የሚፈጠር መኾኑን ነው የገለጹት።

በበጀት ስሚ መርሀ-ግብሩ የክልሉ ግብርና ቢሮ እንዲሁም ተጠሪ መስሪያ የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀታቸውን አቅርበው እያስገመገሙ ይገኛል።

በበጀት ስሚ መድረኩ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቤቴልም ዳንኤልን ጨምሮ ሌሎች ተግባሩ የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *