ከክልሉ ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ መምህራን በቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

Spread the love

”ትውልድ በመምህራን ይቀረጻል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል ክልላዊ ማጠቃለያ የመምህራን ውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ በዛሬው ቀን ይካሄዳል።

ክልላዊ ማጠቃለያ የውይይት መድረክ ተሳታፊ ከክልሉ ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ መምህራኖች ከውይይቱ አስቀድመው የቦንጋ ከተማ ቢሻው ወልዴ ዮሐንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የቦንጋ ከተማ ኮሪደር ልማት አካል የሆነዉ የአረንጓዴ ፓርክ ጎብኝቷል።

መምህራኖቹ፤ ቢሻው ወ/ዮሐንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጎበኙ ሲሆኑ በትምህርቱ በካፋ ዞን አስተዳደር እና በዞኑ ልማት ማህበር ትብብር የተቋቋመ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲሁም በትምህርት ቤት ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውን የቤተመጽሐፍት ግንባታ ምልከታ አድርገዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ቅርብ ክትትል የተገነባው የቦንጋ ኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአረንጓዴ ፓርክ ተዘዋውረው ተመልክቷል።

በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘዉዴን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የቦንጋ ከተማ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከክልሉ ከሁሉም አከባቢዎች የተወጣጡ መምህራን ተሳትፈዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *