የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እየሳበ ነው

Spread the love

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እየሳበ ነው አሉ፡፡

በኢትዮጵያ እና ቤልጂየም የኢንቨስትመንት ዘርፍ ትብብር ላይ ያተኮረ የቢዝነስ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ አህመድ ሺዴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እየሳበ ነው ብለዋል፡፡

10 የሚጠጉ የቤልጂየም ኩባንያዎች የተሳተፉበት የልምድ ልውውጥ መድረክ የዚህ ፍላጎት አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ ኩባንያዎቹ ከሀገር ውስጥ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በቢዝነስ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት 120 ዓመታት የተሻገረ ግንኙነት እንዳላቸው ያስታወሱት በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር አኔሊስ ቬርስቲቼል በበኩላቸው፥ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የኢንቨስትመንት ዕድሎች መስፋታቸውን ተናግረዋል፡፡

በቢዝነስ መድረኩ ላይ የቤልጂየም ኩባንያዎች በግብርና፣ በታዳሽ ሀይል፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በፕላስቲክ መልሶ ማልማት ልምዳቸውን ያካፍላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *