


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኃይል ግንኙነት የመሪነቱን ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚነስትሩ ይህን ያሉት፤ በአዲስ አበባ መካሄዱን በጀመረው አራተኛው የናይል ውኃ ምክንያታዊና ፍትሐዊ አጠቃቅም ጉባዔ /አፍሪራን/ ላይ ነው።
ጉባዔው ቀጣናዊ የኃይል ግንኙነት ለሁሉም እና ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተደረገ የሚገኘው።
የኃይል ግንኙነት የተመድ 2030 እና የአፍሪካ 2063 የልማት ግቦችን ለማሳካት ጉልህ ሚናን ይጫወታል ነው ያሉት ሚንስትሩ።
የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፤ ቀጣናዊ የኃይል ውህደት ከአሁን በኋላ የሩቅ ምኞት አይደለም ብለዋል።
አካታች የሆነ እድገት እና ቀጣናዊ ውህደት እውን የሚሆነው አስተማማኝ የኃይል ምንጮች በዘላቂነት እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ላይ የተመሰረቱ ሲሆን እንደሆነም ነው ዳይሬክተሩ የጠቆሙት።
ጉባዔውን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፤ በመድረኩ ላይ የናይል ተፋሰሱ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ፣ተመራማሪዎችና እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ተገኝተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
