‎ወጣቶች የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን በሕዝብ ዘንድ የማስረጽና የማጽናት መሠረት እንዲያዝ የሚያስችሉ ሥራዎችን በትኩረት መስራት ይገባል ፦ አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

‎ወጣቶች የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን በሕዝብ ዘንድ የማስረጽና የማጽናት መሠረት እንዲያዝ የሚያስችሉ ሥራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ።

‎የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ለወጣቶች እየሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

‎በስልጠናው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደገለጹት ወጣቱ ትውልድ የብሔራዊነት ትርክትን ምንነትና የግንባታ ሂደቶቸን በአግባቡ ተረድተው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስቻልን ዓለማ ያደረገ ነው።

‎ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን ፖለቲካዊ ስብራቶች የተነሳ ከወረሳቸው ውርስ ዕዳዎች ውስጥ ዋነኛው ገዥ ሀገራዊ ትርክት አለመገንባቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎በዚህም ፓርቲው የፖለቲካ ስብራቶችን ለመጠገን አዲስ ሁሉንም የሀገራችን ህዝቦች የሚያሰባስብ ፣አካታች፣ለሁሉም ማንነቶች አመች የሆነ ገዥ ሀገራዊ ትርክት ለመገንባት በርካታ ስራዎችን እየተሰራ ይገኛል።

‎ጽንፍ የያዙ ትርክቶች በጋራ የወደቅንባቸው አክሳሪ ትርክቶች መሆኑን የገለጹት አቶ ነጋ እነዚህ ትርክቶች ጉድለቶች የብሔራዊነት ገዥ ትርክት እንዲፈጠር ገፊ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

‎ከፋፋይ እና አሉታዊ ትርክቶችን የመከላከል ሥራ ምሉዕነት የሚኖረው የህብረ ብሔራዊነትን ማዕከል ያደረገ የብሔራዊነት ትርክትን በሚገባ በማስረጽ ጽኑ መሠረት ማስያዝ ስቻል ነው።

‎በዚህም ወጣቶች የብሔራዊነት ገዥ ትርክት የበላይነቱን እንዲይዝ የጋራ ትናቶችን፣ዛሬን እና የጋራ ነገያችን ላይ በትኩረት በመስራት የጀመርነውን ሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ብርቱ ትግል ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።

‎ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር መፍጠር ፣ጠንካራ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ አቅም በመገንባት ሁሉን አሰባሳቢ የገዥ ትርክት ግንባታን ለማፋጠን ወጣቶች በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

‎የሕዝቦችን አብሮነትና አንድነት በማጠናከር፣ ወንድማማችነትና አህትማማችነት እሴቶችን ይበልጥ በማጎልበት የጋራ አስተሳሳሪ ትርክትን አጠናክሮ በማስቀጠል የጋራ ሀገር፣የጋራ ብልጽግና ለመገንባት በቁርጠኝነት መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።

‎ወጣቱ ከምንም ጊዜ በላይ አፍራሽ ትርክቶችን በማረም የአርበኝነት ስሜትን በመላበስ የብሔራዊነት ገዥ ትርክት ጎልቶ እንዲወጣ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *