ለብዙ ዓመታት ተደብቀው የነበሩ ሀብቶችን በመግለጥ ለሀገር እና ለትውልድ በሚጠቅም መልኩ እየለሙ ነው – የኪነጥበብ ባለሙያዎች

Spread the love

ለብዙ ዓመታት ተደብቀው የነበሩ ሀብቶችን በመግለጥ ለሀገር እና ለትውልድ በሚጠቅም መልኩ እየለሙ መሆኑን፤ የቱሪዝም መዳረሻወችን የጎበኙ የጥበብ ባለሙያዎች ገለጹ።

የጥበብ ባለሙያዎቹ ይህን ያሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት በዳውሮ ዞን የተገነባውን የሀላላ ኬላ ሎጅ ከጎበኙ በኋላ ነው።

የጥበብ ባለሙያወቹ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለሀገር ኢኮኖሚ ፋይዳ ባለው መልኩ ለአገልግሎት ክፍት የሆነውን፤ የሀላላ ኬላ ሎጅን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራወችን ጎብኝተዋል።

በዚህም በሩቅ ከሚሰሙት ይልቅ በአካል መጥተው እነዚህን ትውልድ የሚዋጁ የልማት ስራዎች መመልከት መቻላቸው እንዳስደሰታቸውም ገልጸው፤ እንደ ሀገር ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ከተሰራ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል የተመለክተናቸው ፕሮጀክቶች አስረጂ ናቸው ብለዋል።

ሀገር የሚገነባው ቀደምት አባቶቻችን አስቀምጠው ያለፏቸውን ታሪኮች ለትውልድ በማስተላለፍ በመሆኑ፤ የተሰሩት የልማት ሥራዎች ከኢትዮጵያውያን አልፎ ታሪኩን ዓለም እንዲያውቀው በማድረግ ረገድም ሚናቸው ትልቅ መሆኑን ነው ያነሱት።

በቀጣይ እነርሱም በሙያቸው ሀገር የምትጠብቅባቸውን ሥራ ለማበርከት የተመለከቷቸው የልማት ስራዎች የበለጠ መነሳሳት እንደፈጠሩባቸውም ነው የገለጹት ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *