የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ሆነ

Spread the love

እድሳት ተደርጎለት ላለፉት 4 ወራት በሙከራ ስራ ላይ የቆየው የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡

ቤተመንግስቱ ጥንታዊ ተሽከርካሪዎችና መካነ እንስሳትን ጨምሮ በውስጡ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ሲሆን፥ ደረጃቸውን የጠበቁ ሬስቶራንቶችና ስፓዎች ይገኙበታል፡፡

ሙዚየሙ ክፍት መደረጉን አስመልክተው የብሔራዊ ቤተመንግስት ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ደሬሳ በሰጡት መግለጫ፥ ቤተመንግስቱ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ለማላቀቅ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡

የብሔራዊ ቤተመንግስቱ ሙዚየም ከማክሰኞ በስተቀር ሳምንቱን ሙሉ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 11:30 ለህዝብ ክፍት ይሆናል ብለዋል፡፡

ከጎብኚዎች የሚገኘው ገቢ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ቀሪ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ያግዛል ተብሏል፡፡

የመግቢያ ዋጋ መደበኛ 3 መቶ ብር እንዲሁም ለልዩ ትኬት 1 ሺህ ብር መሆኑንም ነው አቶ ምትኩ የገለጹት ሲል ኤፍኤምሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *