sdfv

Spread the love

በዞኑ የበልግ ወቅት የእርሻ ስራ ውጤታማ እየሆነ እንደሆነ ተነገረ

በምዕራብ ኦሞ ዞን በሁሉም አካባቢዎች የበልግ ወቅት

የእርሻ ስራ ውጤታማ እየሆነ እንደሆነ የዞኑ የግብርና፣ ደን፣ አከባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ገልጿል።

ክልሉ ከያዘው የበልግ ወቅት የእርሻ ስራ እቅድ 35-40 በመቶ የሚሆነው የሚሸፈነው በምዕራብ ኦሞ ዞን መሆኑንም የዞኑ ግብርና፣ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መልኬ ገላጋይ ተናግረዋል።

በዞኑ 125,156 ሄክታር በአዝርእት ሰብሎች፤ በቀቆሎ፣ ማሽላ፣ ሰሊጥና መሰል ምርቶች ለመሸፈን እንዲሁም በሆርቲካልቸር ወደ 6,700 ሄክታር በድምሩ 131,856 ሄክታር መሬት በበልግ እርሻ ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አቶ መልኬ ለሚዲያችን አስረድተዋል።

በዕቅዱ የቴክኖሎጂ ድርሻ 11.2 በመቶ መሆኑን የገለጹት አቶ መልኬ በቆላማው የዞኑ ክፍሎች የአየር ሁኔታ ለውጥ መኖሩ ተግዳሮት የነበረ ቢሆንም ከአምናው በተሻለ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ከበልግ ወቅት የእርሻ ስራ ከ4.5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ዕቅድ ተይዞዐወደ ተግባር መገባቱም ተገልጧል።

በመጨረሻም ከአልሚ ባለሃብቶች ጋር በመተባበር በሀገር ደረጃ ያለውን የምርጥ ዘር እጥረት ማነቆ ለመፍታት ቢ-ኤች140ና ዲኬ77 የተባሉ የምርጥ ዘር አይነቶች እየተባዙ መሆኑንም አስገንዝበዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *