








ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ተወካዮች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ሀሳብ አመንጭነት የተገነባውን የሃላላ ኬላ ሎጂ ለመጎብኘት ወደ ዳውሮ ዞን ገቡ።
የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ ወደ ዞኑ ስደርሱ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ ለሌች የዞንና የሎማ ቦሳ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በስፍራው ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
በአቀባበል ስነስርዓቱ፥ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደገለጹት “በጉብኝታችሁ ፀጥታው ጥበብን ለማፍለቅ ምቹ ሲለሆነ ኢትዮጵያን የሚያስተሳስር ሥራ ሰርታችሁ በኢኮኖሚ ረገድም ጥበብ ፈጠራን፣ ቱሪዝምን እና ስራ ፈጠራን ላይ አይተከ ሚና መጫወት እንዳለባችሁ አሳስበዋል” ተብለዋል።
የዳውሮ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታሪኩ አካሉ በበኩላቸው፥ የሃላላ ኬላ ሌጅ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሳብ አመጭነት የተገኘ ፀጋችን ነው በማለት ይህ ፀጋን በማስተዋወቅ እና በጥበብ ኢትዮጵያን በማስተሳሰር የዜግነት ግዴታን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
“ሀገርና ጥበብ ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ሀገራዊ ውይይት ተሳታፊ የኪነጥበብ ተወካዮቹ በተለያዩ ደረጃ እየተካሄደ በመጣው ውይይት ይህ በጥበብ ዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ቆይታችሁ ያማረና የሰመረ እንድሆን ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።
ኪነጥበብ ባለሙያዎቹ በቆይታቸው በዞኑ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችንና ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን እንደሚጎበኙ መገለጹን የዳውሮ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል
