‹‹‹‹‹‹ ሪፖርታዥ ››››››

Spread the love

የግብርና ዘርፍ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ውስጥ ከሚበረክተው ድርሻ አኳ ከፍተኛውን የሚሸፍንና የኢኮኖሚ መሠረት በመሆን ለማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክት የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ነው።

የግብርናው ዘርፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በዘላቂነት የማሳደግ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን እውን የማድረግ ድርብርብ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል። በመሆኑም በቀጣዮቹ ዓመታት የሚኖረውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሀገሪቱን ሕዝብ የመመገብና ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ በመካከለኛ ጊዜ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ የማስገኘት፣ ለኢንዱስትሪውና ለሌሎች ዘመናዊ ዘርፎች በቂ ግብዓትና የሰው ኃይል የማቅረብ፣ ለሌሎች ዘርፎች ምርቶች ገበያ ወይም ፍላጎት የማጎልበትና በስፋት የሥራ ዕድል የመፍጠር ሥራ ከግብርናው ዘርፍ እንደሚጠበቅ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ይገልጻል ፡፡

ከሀገራዊ የግብርና ግብ መነሻ በማድረግ በክልሉም በግብርናው ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ተቸባጭ ለውጦች እየተመዘገቡም ይገኛል ፡፡ የግብርናው ዘርፍ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ትልቅ ቦታ ኖሮት እየተሰራ ይገኛል ፡፡ በሸካ ዞን ከክልሉ ምስረታ ወዲህ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በግብርናው ልማት ስራዎች ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ፡፡

እንደ ሸካ ዞን በመኸር፣በመስኖና በበልግ የግብርና ልማት ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ለውጥ እየተመዘገበ እንደሚገን አቶ አበበ ማሞ የሸካ ዞን ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል ፡፡ በዞኑ በየኪ ወረዳ የማሽላና ሩዝ ሰብሎች በስፋት የሚለሙበት አካባቢ ነው ፡፡

በደጋማው አካባቢ በባቄላ፣አተርና ጤፍ ሰብሎች በስፋት እየተሰራ እንደሚገንም አቶ አበበ ተናግረዋል ፡፡ በዞኑ ተረጂነትንና ልመናን ለማስቀረትም ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛልም ብለዋል ፡፡

በዘንድሮው የመኸር ግብርና ልማት ስራዎች በአዝዕርትና በሆልቲካልቸር ሰብሎች ከ18 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ግብ የተያዘ ሲሆን በኢኒሼቲቭ ከተያዙ ሰብሎች መካከል በሩዝ ሰብል 3 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚለማ አቶ አበበ ገልጸዋል ፡፡

ዞኑ ካለው እምቅ የመልማት አቅም 5 ቀበሌዎችን አቅፎ በያዘው የኪ ወረዳ ባለፈው መኸር የእርሻ ወቅት በሩዝና ማሽላ ሰብሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ውተታማ ተግባራት መከናወናቸውን አቶ አበበ ተናግረዋል ፡፡

በክላስተር እርሻ በወረዳው ከ500 ሄክታር በላይ ሩዝ መከናወኑን የገለጹት አቶ አበበ በማሽላ ሰብል ላይም አርሶ አደሩን በማበረታታት በክላስተር ለማልማት በመኸር የግብርና ልማት ስራዎች ግብ መያዙንም አስረድተዋል ፡፡

በደጋው አካባቢ በሚለሙ ሰብሎችም በርካታ ተግባራት መከናወን መቻላቸውንም አቶ አበበ ተናግረዋል ፡፡ በዞኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች በስፋት በማልማት አርሶ አደሮችን በኢኮኖሚው ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩም ይገኛል ብለዋል ፡፡

በዚህም በበልጉ ከ7 ሺህ በላይ ሄክታር በማልማት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት በዘርፉ መገኘቱንም አስረድተዋል ፡፡

ዞኑ ከሚለሙ የሆልቲካልቸር ሰብሎች በተለይም በቀይ ስር ፣ጥቅል ጎመን፣ ድንች እና በመሳሰሉ ሰብሎች በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውን አቶ አበበ ተናግረዋል ፡፡

ከዞኑ በቀን ከ20 የማያንሱ ትላልቅ መኪናዎች ወደ አዲስ አበባ ምርቱን እንደሚያጓጉዙም አቶ አበበ የገለጹ ሲሆን ይበልጥ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተለይ በድንች ልማት ስራው የበለጠ በክላስተር አርሶ አደሩ እንዲያለሙ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፡፡

አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን የገበያ ትስስርን ከመፍጠር አኳያ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት በአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ወደ ሌላ አካባቢ በማውጣት እና በመሸጥ እንዲጠቀሙ ይደረጋልም ብለዋል ፡፡

በዞኑ ውስጥ በተለይም አትክልትና ፍራፍሬ በስፋት ከሚመረትበት ማሻ አካባቢ ወደ ቴፒ ከተማ በማቅረብም በሰንበት ገበያዎች ምርቶችን በማቅረብ ህብረተሰቡ ተተቃሚ እንዲሆንና አርሶ አደሩም በኢኮኖሚው ተተቃሚ እንዲሆን ትኩረት በመስጠት ይሰራልም ብለዋል ፡፡

ከድንች ጋር በተያያዘም ከዚህ ቀደም በስፋት ምርቱ ይመረት እንደነበርና የገበያ ትስስር በመጥፋቱ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ መሆን ወደ ማይችልበት ደረጃ ደርሶ እንደነበር ያወሱት አቶ አበበ አሁን ላይ ወደ ሀገሪቱ የተለያ አካባቢውች ምርቱን በማጓጓዝ እንዲሁም ከድንች ችብስ ፋብሪካ ጋር በማገናኘት ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ስራዎች እየተከናወኑም እንደሚገኝ አስረድተዋል ፡፡

የድንች ሰብልን በስፋት በክላስተር ደረጃ በማምረት በቂ ምርት በመያዝ በዞኑ የድንች ችብስ ፋብሪካ እንዲቋቋም ጥረቶች እየተደጉ እንደሚገንም ገልጸዋል ፡፡

በሌሎች የሆልቲካልቸር ሰብሎች በዞኑ ደጋማ አካባቢዎች በስፋትና በጥራት በኩታገጠም አስተራረስ አርሶ አደሮችን ግንዛቤ በመፍጠር በዚህ የመኸር ግብርና ልማት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ብለዋል አቶ አበበ ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *