




በሀገር ደረጃ ለ3 ተከታታይ ቀናት ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደ ሀገር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ ለማድረግ እንደሆነ ለማድረ ያለመ መሆኑን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ገልጸዋል።
ባለሙያዎቹ ወደ ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበል ወቅት የዞን አመራር አካላትና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
ባለሙያዎቹ በቆይታቸው በዞኑ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችንና ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ፋንታሁን ብላቴ የተመራው የኪነጥበብ ባለሙያዎች ቡድን ኮንታ ዞን መግባታቸዉን የ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
