የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገ ሥራ ይጠበቃል:-አቶ አልማው ዘውዴ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የማህበራዊ ክላስተር ተቋማት የ2016 በጀት አመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተግባር የተደገፈ ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የግምገማ መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ጠንካራ አፈፃፀሞችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በጉድለት የተገመገሙ አፈፃፀሞችን በመለየት በልዩ ትኩረት ለማከናወን የሚያስችል እንደሆነ ተብራርቷል።

በመድረኩ የተገኙ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ደነቀ ማሞ ያልተሳኩ ተግባራትን በቀጣይ ለማረምና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የክላስተሩ አመራሮች ችግሮችን ውስጣዊ በማድረግና የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ልሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በጤና ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይ በክልሉ እየተስተዋለ የሚገኘውን ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉ አቀፍ ድጋፍና ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተብራርቷል።

በትምህርት ዘርፍ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን በክልሉ የተጀመሩ ተግባራት ለውጥ እያመጡ ቢሆንም የሚፈልገውን ውጤት ለማስመዝገብ የሚደረጉ ጥረቶች ይበልጥ ልጠናከሩ ይገባልም ተብሏል።

በክልሉ በትምህርት ለትውልድ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ 158 የአንደኛ ደረጃ ፣18 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ማሳደስ መቻሉና 488 አዲስ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባታቸው ተገልጿል።

በክረምትና በጋ ወራት በመደበኛ የበጎ ፍቃድ አገለግሎት ከ605 ሺ በላይ ወጣቶችንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጋ የማህበረሰብ ክፍሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በቱሪዝም፣ በቅርስ ጥበቃ፣ በእደ ጥበብና በባህል ዘርፍና በስፖርት ዘርፍ በክልሉ ለሚገኙ 1473 ዘጎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ከማልማት አንፃር በቀጣይ በልዩ ትኩረት ልሰራ ይገባል ተብሏል።

በባለፉት ስድስት ወራት የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ዋስትና ቢሮ እንዲሁም ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ ያከናወኗቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *