

ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የወጪ ንግድ ገቢያችን ዋልታም ነው ብለዋል።
በርካታ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚሳተፍበት ዘርፍ በመሆኑ ትልቅ ስፍራ እንዲሰጠው መደረጉን ጠቁመዋል።
ይህም በመሆኑ ግብርና ቢዚህ ዓመት 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ መታቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የግብርናው ዘርፍ ከሌሎች ዘርፎች ልዩ ትኩረት ያገኘው ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ማግኘት አለባት፤ አምርታ መብላት ያልቻለች ሀገር ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማረጋገጥ ትቸገራለች በሚል የምግብ ሉዓላዊነትነ ለማረጋገጥ ግብ ይዘን ሰርተናል” ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት 27 ሚሊዮን በሴፍቲኔት የተያዙ ዜጎች ከሴፍቲኔት ለማሸጋገር ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ነጻ መውጣታቸውን ገልጸዋል።
ይህ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ማሳያ ስለሆነ ኩራት ሊሰማን ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀሪው ከ4 ሚሊዮን ያላነሰ ተረጂም ነጻ በማውጣት ኢትዮጵየን ሙሉ ለሙሉ የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ማድረግ አለብን ብለዋል።
