በህብረተሰብ ተሳትፎ በቴፒ ከተማ የተገነባዉ የጎጂ ድልድይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ድልድዩን መርቀዋል።

የጎጂ ድልድይ በህዝቡ ብርቱ ትብብር የተሰራ የህዝቡ አንድነት ማሳያ ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል።

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት በህዝቡ ብርቱ ትብብር የተሰራ የህዝቡ አንድነት ማሳያ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

ህዝቡ ጉልበቱን፣ሀብቱንና ዕውቀቱን በማስተባበር የመንግስት አቅም በመሆን ላከናወኑት ተግባር በክልሉ መንግስት ስም አመስግነዋል ።

ይህ የልማት ተነሳሽነት በሌሎች ልማቶችም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ።

የተገኘውን አውንታዊ ሠላም ማጽናት እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ አሁን የመጣዉ ልማት የሠላም ውጤት ነውም ብለዋል።

በአካባቢው በእጥረት የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ችግር የክልሉ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ምላሽ ይሰጣል ብለዋል።

የአካባቢውን ህብረተሰብ በማሳተፍና በዞን ውስጥ ያሉ መዋቅሮችን በማስተባበር 20 ሜትር ርዝመት 6 ሜትር ስፋት 4ሜትር ከፍታ ያለው ድልድይ ነው መሆኑን የተናገሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ናቸው።

ግንባታው ሶስት ዓመት የፈጀ ሲሆን 12.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖበታል ብለዋል።

የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ወንድሙ ግርማ ባስተላለፉት መልዕክት የመዣንግ ብሔረሰ መሠረታዊ ጥያቄ የመለሰ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

የጎጂ ድልድይ አዲስ ብርሃን ቀበሌንና ሰላም ቀበሌን የሚያስተሳስር ለከተማው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ገልጸዋል ።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታን ጨምሮ፣የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣የክልል፣ የሸካ ዞን እና የቴፒ ከተማ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *