
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሐምሌ 14_16/2017 ዓ.ም ድረስ በታርጫ ከተማ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ገልጸዋል።
ከጉባኤው ጋር በተያያዘ ለሚዲያችን መግለጫ የሰጡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለጉባኤው ስኬታማነት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።
በጉባኤ የ2017 በጀት አመት የአስፈጻሚ አካላት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትና ሌሎች አጀንዳዎች ቀርቦ ወይይት እንደሚደረግም አንስተዋል።
የምክር ቤቱ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ከሐምሌ 13/2017 ጀምሮ ወደ ታርጫ ከተማ እንደሚገቡ የገለፁ ዋና አፌ ጉባኤ ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ የባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
