




ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት ሪፖርት በመሠረተ ልማት ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርርዋል ፡፡በዚህም ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፡-
በሸካ ዞን የእርምጭ ኩቢጦ አዲስዓለም ምዕራፍ አንድ እና በካፋ ዞን የተቺቢ ቀበሌ ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ 8,573 ህብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
የቦባ ገጫ የንጹህ የመጠጥ ዉሃ ግንባታ አፈፃፀም 82% መድረስ መቻሉን ተጠቅሷል።
በባስኬት ፈንድ በቱም ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ 10,052 ህብረተሰብ ተጠቃሚ ሆኗል፡፡
በዳውሮ ዞን የያሎ ላላ ከተማ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 99% በማድረስ የመስመር ፍተሻ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በፕሮግራሙ በክልሉ በርካታ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ቢሆንም የታችኛው መዋቅሮች የወጪ መጋራት ድርሻቸውን እስካሁን መፈጸም አለመቻሉ እንደጉድለት ተነስቷል።
በዘላቂ የልማት ግቦች ማሳኪያ/SDG/ የግዝ መሬትና ሽሚ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት፣ በሸካ ዞን የሻዬ ምንጭ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እና በካፋ ዞን የኦሚያ ቀበሌ ንጹህ የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ 11,712 የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በጌሻ ወረዳ የዳካ ከተማ መጠጥ ዉሃ ጥገናና ማስፋፊያ እንዲሁም የሰሜን ቤንች ወረዳ የቲሹ ቀበሌ የመጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ 7,309 ማህበረሰብ ተጠቃሚ ሆኗል።
በማዕድን ሃብት ልማት ስራዎችን በሚመለከት 135 አዲስ የማዕድን ፈቃድ ለመስጠትና ነባር ፍቃድ ለማደስ ታቅዶ መከናወን መቻሉ፣
155.35 ኪ.ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ በማቅረብ ከዕቅዱ (51.8%) ማሳካት ተችሏል፡፡
ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚውሉ 168,720 ቶን የድንጋይ ከሰል ማምረት ተችሏል፡፡ ከፈቃድ፣ ከሮያሊቲ ገቢ እና ከማዕድን ስራዎች 217,742,380 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡
ከመስኖ ልማት ግንባታ የዳማ ፌዝ አንድ እና የማራጫ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች የግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር በክልሉ እየተገነቡ ያሉ 3 መናኃሪያዎች አፈጻጸማቸው የሚዛን 75% ፣ የታርጫ 85%፣ እንዲሁም የቦንጋ 70% ማድረስ ተችሏል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎት ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከማድረግ ለ4521 ተሸከርካሪዎች ድንገተኛ የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ ተደርጓል።
የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ለ1,336,886 የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ተችሏል፡፡
በሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍ፣ የድልድይ ግንባታ አቅርቦትን ከማሳደግ ረገድ የጉሚ ድልድይ የግንባታ 80%፣ የቡቃ ድልድይ የግንባታ 100%፣ የኪሉ ድልድይ ፕሮጀክት 95% እንዲሁም፣ የሾር ድልድይ ፕሮጀክት 95% ማድረስ ተችሏል፡፡
የመንገድ ግንባታ አቅርቦትን ከማሳደግ ረገድ በካፋ ዞን ሸዳ ማልጋዊ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 11 ኪ.ሜ ጥገና 13 ኪ.ሜ ግንባታ በድምሩ 24 ኪ.ሜ ተከናውኗል፡፡
በዳውሮ ዞን ገሳ-ቤሮ ያማላ ከ5.84 ኪ/ሜ ውስጥ 80% የመንገድ ሥራ ተከናውኗል፡፡
በቤንች ሸኮ ዞን ፃት ጎሚቃ ውል ተቋርጦ በአዲስ ተቋራጭ ከ8.89 ኪ/ሜ ውስጥ 4.4 ከ.ሜ (50%) የመንገድ ስራ ማከናወን ተችሏል፡፡
በህብረተሰብ ተሳትፎ 185.7 ኪ/ሜ የመንገድ ከፈታ፣ 38.2 ኪ/ሜ የመንገድ ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን በግንባታና ጥገና ስራ ከህብረተሰብ ተሳትፎ ብር 312,500,000 መሰብሰብ ተችሏል፡፡
በመንዶች ባለስልጣን በሚዛን ዲስትሪክት:- በ5 ፕሮጀክቶች (164 ኪ.ሜ) የመንገድ ግንባታ ስራ የተስራ ሲሆን ሌሎች ግንባታዎች በተደረገው ሁሉ አቀፍ ድጋፍ በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል ።
በታርጫ ዲስትሪክት ፡- 2 ፕሮጀክቶች (42 ኪ.ሜ) የመንገድ ግንባታ ማከናወን የተቻለ ሲሆን ሌሎች በግንባታ ሂደት ላይ ይገኛሉ።
በቦንጋ ዲስትሪክት- 5 ፕሮጀክቶች (136 ኪ.ሜ) የመንገድ ግንባታ ስራ መከናወን እንዲሁም በግንባታ ሂደት ላይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል ።
179 ተማሪዎች በሆስቴሎች ትምህርታቸውን በመከታተል እንዲችሉ ተደርገዋል ።
የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ በመጀመሪያ ዲግሪ 116 እና በዲፕሎማ 42 ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑ፣
የመኤንት ሻሻ ወረዳ ኮምፒሪሄንሲቭ ጤና ኬላ ግንባታ 100% በማጠናቀቅ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ማሟላት ተችሏል ፡፡
በ4 ወረዳዎች 12 አነስተኛ የምንጭ ግንባታ በማጠናቀቅ 8,696 የማህበረሰብ ክፍሎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸዉ።
18 ኪ/ሜ ከባቹማ እስከ ጨበራ DC-2 የጠጠር መንገድ ግንባታ በማጠናቀቅ አገልገሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።
44 ኪ/ሜ ሀዱባ-ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሶስት መንገድ ከፈታ ሥራ 100% ማድረስ ታቅዶ ተከናውኗል፡፡
ከ150 ሄ/ር በላይ ሊያለማ የሚችል የኪሉ አነስተኛ መስኖ ከነበረበት 65% ወደ 85% ማድረሰ ተችሏል፡፡
በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ 915.5 ሄ/ር የለማ መሬት መዘጋጀቱ ፤ 855.7 ሄ/ር መሬት ለተለያዩ አገልግሎቶች በምደባና በጨረታ ማስተላለፍ መቻሉን፣
ሳይፈቀድ የተያዘ ይዞታ ህጋዊ ሥርዓት እንዲይዝ ከማድረግ አንጻር 27,526 ይዞታዎች ወደ ህጋዊ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
የመሠረተ ልማት ስራዎች አንጻር አዲስ መንገድ ከፈታና ጠረጋ 298.2 ኪ/ሜ፣ የጠጠር መንገድ ግንባታ 118.3 ኪ/ሜ፣
በህዝብ ተሳትፎ ከህብ/ሰቡ ከ150.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብ፣ የጉልበትና ዓይነት በማሰባሰብ የተለያዩ የልማትና የመሠረተ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል።
221 የግንባታ ፕሮጀክቶች ጥራት ቁጥጥርና ክትትል መደረጉ፣ ግንባታቸዉ የተጠናቀቁ 72 ፕሮጀክቶች ጊዜያዊ ርክብክብ ማድረግ ተችሏል፡፡
በጌታሁን ግርማ
