የቀጠለዉ የርዕሰ መስተዳድሩ ሪፖርት

Spread the love

በማህበራዊ ልማት ዘርፍ

የትምህርት ልማት ስራዎች

👉በትምህርት ለትውልድ ኢንሸቲቭ ከማህበረሰብ ተሳትፎ የትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሻሻል በተሰራው ስራ 711,748,341 ብር ማሰባሰብ ተችሏል።

👉በተሰበሰበው ሀብት 661 አዲስ መማሪያ ክፍሎች መገንባቱ፣ 1,417 ነባር መማሪያ ክፍሎችን የጥገና ስራ ተከናውኗል፡፡

👉በክልል ደረጃ በልዩ ንቅናቄ 36 ደረጃቸውን የጠበቀ ሞዴል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ግንባታ የሚሆን 185,527,812 ብር በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

👉በአርብቶ አደር አካባቢ የትምህርት ተደራሽነትን ለማሻሻል የቱልጊት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በኩል በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ግንባታው ተጠናቆና የውስጥ ቁሳቁስ ተሟልቶ በ2018 ትምህርት ዘመን ትምህርት ለማስጀመር ዝግጁ ተድርጓል፡፡

👉በቅድመ አንደኛ 101,300፣ በአንደኛ ደረጃ (ከ1ኛ-6ኛ) 476,589፣ (ከ7-8ኛ) 83,651 እና በሁለተኛ ደረጃ 87,332 በድምሩ ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል 748,872 የዕወቅዱ (79%) በመመዝገብ የመማር ማስተማር ሥራ ተከናውኗል፡፡

👉በ349 ትምህርት ቤቶች 44,312 ተማሪዎችን ምገባ ማድረግ ተችሏል፡፡

👉የትምህርት ግብዓት አቅርቦት እና ቴክኖሎጂ ስርፀትን ከማሻሻል አንጻር የተለያዩ መጽሐፍት በመሰራጨት ላይ መሆኑ፤

👉ጥምርታውን ለማሻሻል ተጨማሪ 885,000 መጽሐፍት ከቅድመ 1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በመታተም ላይ ይገኛል፡፡

👉ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከ9-12ኛ ክፍል መጽሀፍት 1፡1 በሆነ ጥምርታ ለተማሪዎች ተደራሽ ተደርጓል።

👉የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እጥረት ለመቅረፍ 608 አዲስ ዲፕሎማ እና 231 ሰርተፊኬት ዕጩ መምህራን ስልጠና መጀመራቸው፡፡

👉የመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ብቃት እየመዘኑ የአቅም ማጎልበቻ አማራጮችን ለመዘርጋት በተያዘው ዕቅድ 11,612 እንዲመዘኑ ተደርጓል፡፡

👉በ2017 ዓ.ም በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ48,072 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተሰጥቷል፡፡

👉38,688 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ፈተና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

👉በ2016 ዓ.ም በክልል ደረጃ ሀገራዊ ፈተና ከወሰዱ 16,872 መደበኛ ተማሪዎች መካከል በመደበኛና በሪሜዲያል 1,953 ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል፣

👉 በ2017 ዓ.ም በጠቅላላው 19,127 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

የጤና ሥራዎችን በተመለከተ

👉የወባ ተዋሲያን በደማቸው የተገኘባቸው 1,207,730 አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

👉ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው 42 ወረዳዎች 1,144,762 የአልጋ አጎበር ለማህበረሰቡ ቤት ለቤት ማሰራጨት ተችሏል፡፡

👉በእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት 485,368 ሴቶች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

👉112,655 እናቶች የቅድመ ወሊድ አገልግሎት አንድ (1) የተከታተሉ ሲሆን አራት ጊዜና ከዚያ በላይ ለ 86,482 እናቶች አገልግሎቱን ለማከናወን ተችሏል፡፡

👉በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች 64,435 እናቶች የወሊድ አገልግሎት አግኝተዋል፡፡

👉የደም ባንክ አገልግሎት 5952 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 4732 (80%) ደርሷል፡፡

👉ከማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አንጻር 421,541 አባላት ማፍራቱ መቻሉ፤ የአባላት ምጣኔ ሽፋን 75.6 % ደርሷል፡፡

👉ነባር አባላት እድሳትን 289,696 ለማደስ ታቅዶ 258,776 የማዐጤመ አባላትን በማደስ 89.3% ላይ ይገኛል፡፡

👉አዲስ አባላት 267,711 በአድስ አባል ለማድረግ ታቅዶ 162,765 (60.8%) ማፍራት ተችሏል፡፡

👉በማህበረሰብ ጤና መድን 445,736,763 ብር በመሰብሰብ ባንክ ገብቷል፡፡ ባንክ ከገባዉ ገንዘብ 139,544,607 ብር ወደ ጤና ተቋም ተላልፎ የመድሐኒት ግዥ የተፈፅሟል።

👉12 የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች ተከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛሉ።

ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ

👉153 የቱሪዝም ሃብቶች ልየታና ትንተና ስራ ተከናውኗል፣

👉የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ብቃታቸው በማረጋገጥ እውቅና መስጠት 120 ተከናውኗል ፡፡

👉በስፖርት ዘርፍ ከመንግስት፣ ከህብረተሰብና ከተለያዩ ምንጮች 55,281,189 መሰብሰብ ተችሏል።

👉በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ 27 ሰልጣኞችን በአትሌቲክስ ስፖርት እየሰለጠኑ ይገኛሉ።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ

👉ከከሴቶች መብትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አኳያ ከሴት ልጅ ግርዛትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች 62 ቀበሌዎችን ነፃ ማድረግ ተችሏል፡፡

93647 ሴቶችን በቁጠባ እንዲሳተፉ ተደርጓል ፡፡

👉በክልሉ 82,940 ሴቶች የገጠር መሬት ባለቤትነት ተረጋግጦላቸዋል ፡፡

👉658,315 ወጣቶች በተለያዩ ከክረምት እስከ በጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ ተድርጓል፡፡ 👉ይህም አገልግሎት በገንዘብ ሲተመን ብር 618,020,980 የሚገመት ነው፡፡

👉658,315 ወጣቶች በተለያዩ ከክረምት እስከ በጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ ተድርጓል፡፡ 👉ይህም አገልግሎት በገንዘብ ሲተመን ብር 618,020,980 የሚገመት ነው፡፡

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *