ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ አባላት በአስተዳደር ዘርፍ ሥራዎች የተከናወኑ ተግባራት አቅርበዋል።

Spread the love

የሠላምና ፀጥታ ስራዎች

👉የክልሉን ሠላም ለማጽናት 491,389 የህብረተሰብ ክፍሎችን በሰላም፣ በብዝሃነት፣ በአብሮነትና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ተችሏል ፣

👉60 የሰላም ምክር ቤቶችን በማጠናከር ወደ ስራ ለማስገባት ተችሏል።

👉 የሃይማኖት ተቋማት ለሁለንተናዊ ሠላም ግንባታ ያላቸው ሚና ለማሳደግ

👉32 የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አደረጃጀቶችን ለማጠናከርና መደገፍ ስራ ተሰርቷል ፣

👉 በየደረጃው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከቀረቡ 63 የሃይማኖት ነክ መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ተችሏል፡፡

👉ከአጎራባች ክልሎች በሚያዋስኑ ዞኖች የሚሰተዋሉ የጸጥታ ሥጋቶችን ለመቀነስና ሠላሙን ለማጽናት 28 ዙር ዙር ምክክር ተደርጓል።

👉39 ከፍተኛ ስጋት ያለባቸውን ቀበሌያትን ወደ አንጻራዊ ሠላም እና 187 መለስተኛ ስጋት የሚስተዋልባቸውን ቀበሌያትን ወደ አስተማማኝ ሠላም ማሸጋገር ተችሏል፡፡

👉የወሳኝ ኩነቶች የምዝገባ ሽፋንን በክልሉ ከሚገኙ 930 የምዝገባ ኮድ ከተሰጣቸው ቀበሌያት መካከል 90% (837 ቀበሌ) ለማድረስ ታቅዶ 837 (100%) ማከናወን ተችሏል፡፡

👉የሚሊሻ አቅም በማጠናከረ በሚልሻ ኃይል በህግ የሚፈለጉ 5,549 ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡

👉የወንጀል መከላከል ሥራውን ውጤታማነት ለማረጋገጥ 3,799 የፖሊስ አመራርና አባላትን መገምገምና ማጥራት ተችሏል፡፡

👉ከግምገማው በመነሳት 55 አመራሮች ከቦታቸው እንዲነሱ፣ 739 አመራርና አባላት በማስጠንቀቂያ፣44 በዲሲፒሊን እንዲጠየቁ፣ 34 አመራርና አባላት ለህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡

የፍትህ ስራዎች አፈጻጸም

👉በሁሉም የወንጀል አይነቶች ለዐቃቤ ህግ 9,195 ቀርቦ አስተያየት እና ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

👉የምርመራ መዝገቦችን የማጥራት ምጣኔ 93.2% ተከናውኗል፡፡

👉7,151 የወንጀል ክስ መዝገቦች ላይ በፍርድ ቤት ክርክር በማሄድ በፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡

👉5,806 መዝገቦች በተከሳሾች ላይ የጥፋኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ፤ 292 መዝገቦች ላይ ተከሳሾች በነጻ እንዲሰናበቱ፣ 1,763 መዝገቦች ለሚቀጥለዉ የዞሩ ናቸዉ፡፡

👉በሙስና ወንጀል ጉዳዮች ለዐቃቤ ህግ 197 መዝገቦች ቀርቦ 189 መዝገቦች ላይ የተለያዩ ህጋዊ አስተያትና ዉሳኔ መስጠት የተቻለ ሲሆን የማጥራት ምጣኔን 95.9% ተከናውኗል፡፡

👉በታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀል 137 መዝገቦች ላይ ህጋዊ አስተያትና ዉሳኔ የተሰጠ ሲሆን የማጥራት ምጣኔ 97.5% ለማድረስ ታቅዶ 95.8% ማድረስ ተችሏል፡፡

👉በሴቶችና ህፃናት የሚፈጸሙ ልዩ ልዩ ወንጀሎች 498 መዝገቦች ምርመራቸዉ ተጠናቆ ለዐቃቤ ህግ የደረሱ ሲሆን በ488 መዝገቦች ላይ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

👉6,470 በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደ ማረሚያ ቤት የተላኩ የቀጠሮ እስረኞችና የሕግ ታራሚዎችን በመቀበል እያስተናገደ ይገኛል፡፡

👉በመታረም ላይ ለሚገኙ 1,327 ታራሚዎች ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል የቀለም ትምህርት እንዲያገኙ ተድርጓል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ስራዎች አፈጻጸም

👉የጸረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል ዕቅድና አፈጻጸም ከመጠን፣ ከጥራት እና ከጊዜ አንጻር በመገምገም 2 ዙር ግብረ-መልስ ተሰጥቷል፡፡

👉ብልሹ አሰራር ዉስጥ የተሳተፉ የመንግሥት ሠራተኞች 238 ሲሆኑ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፣

ህጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸዉ 6 ናቸዉ፡፡

👉በመልካም አስተዳደር ጉድለት 540 አቤቱታ ቀርቦ 534 (98%) ምላሽ እንዲያገኝ ተድርጓል፡፡

👉235 ባለሙያዎችን በ 2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ እንዲከታተሉ በመመልመል ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡

👉በ43 ተቋማት የሰው ኃይል ስምርት 11,185 ተፈትሾ 1,462 ጉድለት የተገኘ ሲሆን ብር 6,094,633 ከብክነት ማዳን ተችሏል፡፡

👉 23,392 የትምህርት ማስረጃ እስካን በማስደረግ ለማሰባሰብ ታቅዶ ለመፈጸም ተችሏል፣

👉የአስተዳደር ፍ/ቤት አፈጻጸም፡- አዲስ የይግባኝ መዝገቦች 141፣ ከባለፈው በጀት ዓመት 02 የተላለፈ በድምሩ 143 መዝገብ ቀርቦ 140 መዝገቦች ላይ ውሳኔ በመስጠት 3 መዝገቦች ወደ ቀጣዩ በጀት ዓመት በቀጠሮ ተላልፏል፡፡

የመንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራዎች አፈጻጸም

👉10 ሁነቶችንና መድረኮችን ለማሰተባበርና ለመምራት ታቅዶ 11፣

👉 የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉን ተወዳዳሪነትንና ውጤታማነትን ለማሳደግ የሕግ ማዕቀፍ 2 የስራ ማኑዋልና መመሪያ ተዘጋጅተዋል፣

👉ቅንጅታዊ አሠራሮችን በመዘርጋት የዲጂታል ሚዲያ ለማሳደግ ለሚዲያ በቋሚነት 24 ሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ አጀንዳዎችን መስጠት መቻሉ፣

👉በሚዲያ ሥራዎች የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ እና የአዝማሚያ ትንተና ለማድረግ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ሚዲያዎችን ለመለየት 5 ታቅዶ 5 ተከናወኗል።

👉በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ 20 ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱ እና 20 ጊዜ ፕሬስ ሪሊዞችን ተሰጥቷል ፣

የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ስራዎች አፈጻጸም

👉ቀልጣፋና ግልፅነት ያለው የአስቸኳይ ሙስናን ከመከላከል ረገድ 729 ጥቆማዎች በፅሁፍ፣ በስልክ፣ በአካል እና የተለያዩ መወበሎ መቻሉ፣

👉ከነዚህ አስቸኳይ መከላከል ስራ የተሰራ 292፣ ለፍትህ አካላት ተላልፎ የተሰጠ 124፣ ምክር አገልግሎት ያገኘ 16፣ ህግ ከለላ እንድሰጥ የተደረገ 11፣

👉ተመዝብሮ የነበረ እና በኦዲት ግኝት ክትትል ተደርጎ ብር 45,618,878.2 ማስመለስ ተችሏል፡፡

👉በአጠቃላይ በአስቸኳይ መከላከል እና በኦዲት ብር 224,490,270.7 ከምዝበራ ማዳን ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *