




በምክርቤቱ ጉባኤ ላይ የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ላይ ከምክርቤት አባላት አስተያየት እና ጥያቄዎች ቀርበዋል።
የምክር ቤት አባላቱ የክልሉ መንግስት አስፈጻሚ አካላት አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ያለ፣የሚታይ ለዉጥ ያለበትና የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበት በጀት ዓመት ነዉ ስሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የምክርቤት አባላት በክልሉ በግብርና ልማት ስራዎችና በሌሎች የልማት ውጥኖች በበጀት ዓመቱ በውጤት የታጀቡ ተግባራት መከናወናቸውን አስተያየት ሰጥተዋል።
ቀድሞ የነበሩ ግጭቶችንም በእርቀ ሰላምና በሀገር ባህል መሠረት እንዲፈቱ መደረጉ የሚበረታታ ስራ መሆኑን አንስተዋል።
የተጠናከረ የሱፐርቪዥን ስራዎች መከናወናቸው ከወረቀት ባለፈ መሬት ላይ ያሉ አፈጻጸሞች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን አመላካች ስለመሆኑ አባላቱ ተናግረዋል ።
የምክርቤቱ አባላት በፌዴራል መንግስት የሚገነቡ መንገዶች እና በክልል መንግስት እየተገነቡና ያላለቁ የመንገድ መሠረተ ልማት ስራዎች እንዲጠናቁቁ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።
በመደመር ትውልድ ቤተመጻሕፍት ግንባታ መነሻነት ልምድ ተወስዶ በክልሉ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች በዚህ ልክ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ጥረት ቢደረግ የተሻለ ይሆናል በማለትም የምክርቤት አባላት አስተያየት ሰጥተዋል።
በከተሞች የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክሮ የሰራበት ይገባልም ብለዋል።
የከተሞች ዕድገት ምጣኔ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ሲሉም የምክርቤት አባላት ጠይቀዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በግብርና ልማት ስራዎች የተሰራው ስራ የሚበረታታ ነው ያሉት የምክርቤት አባላት አሲዳማ መሬትን የማከም ጉዳይ ይበልጥ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
ቡናን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ አቅምን መሠረት ያደረጉ ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባልም ብለዋል።
ኢንተርፕራይዞችን ከማሸጋገር አንጻር አፈጻጸሙ አነስተኛ በመሆኑ በተገቢው ሊሰራበት ይገባልም ብለዋል።
የብድር አመላለስም በትኩረት እንዲሰራ አባላቱ አሳስበዋል።
በትምህርት ለትውልድ ስራዎች የሚበረታቱ ተግባራት በኖሩም ከመመሪያ መጽሐፍት አቅርቦት አሁንም ትኩረት ሊደርግ ይገባልም ብለዋል።
የጤና ቢሮ ሥራዎችን እየደገፈና እየተከታተለ ያለበት ሁኔታ የሚበረታታ ሲሆን በየጊዜዉ መልኩን እየቀያየረ ያለዉን የወባና በሽታ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎች አሁንም ይበልጥ ሊተኮርባቸው ይገባል ብለዋል።
ግንባታቸው የተጀመሩ የክልል ተቋማት ቢሮ በፍጥነት እንዲከናወኑ የክትትል ስራዎችን ማጠናከር ይገባል፣ በጀሙና አመያ ከተሞችም መሰል ግንባታዎችን ለመስራት ምን ታስቧል ሲሉ የምክርቤት አባላት ጠይቀዋል።
ያደሩና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሆኑ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ ለአገልግሎት ብቁ የማድረጉ ስራ የሚበረታታ መሆኑንና ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በምክርቤት አባላት ተነስተቷል።
በከተሞች አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዕጥረት መኖሩ በሚፈለገው መጠን አገልግሎቶችን ማሳለጥ አይቻልም ለዚህም ያለውን ችግር ፈጥኖ ማስተካከል ይገባል ሲሉም የምክርቤት አባላት ጠይቀዋል።
በክልሉ ብዝሃ ከተሞች የተጀመሩ መናኸሪያቸው አፈጻጸማቸው የተሻለ መሆኑን ያነሱት የምክርቤት አባላት በቴፒ ከተማም ካለው የተሽከርካሪ ፍሰት አንጻር ደረጃውን የጠበቀ መናኸሪያ እንዲገነባም ጠይቀዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪ የኃይል እና የብድር አቅርቦት ትኩረይ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
የሚዛን የመጠጥ ዉሃ ችግር ለመፍታት እየተሰራ ያለዉ ስራ ያለበት ደረጃ ቢብራራ የሚል የምክር ቤት አባላት በእነዚህና በሌሎች ዘርፎች ላይ አስተያየት እና ጥያቄዎችን አንስተዋል።
በታጠቅ አበበ
