የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክርቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ 2ኛው ቀን መካሄድ ጀምሯል።

Spread the love

ምክርቤቱ በሁለተኛው ቀን የ2017 ዓ/ም ተጨማሪ የበጀት ረቂቅን መርምሮ አጽድቋል።

የተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ በ2017 በጀት ዓመት ለመንግስት ሰራተኞች የ9 ወራት የደመወዝ ማሻሻያ ክፍያ በጀት መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ አቅርበዋል።

የቀረበው ተጨማሪ በጀት ከክልል ጀምሮ እስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን ወርዶ ተፈጻሚ እንደሚሆንም ተገልጿል።

በተጨማሪ የበጀት ረቂቅ አዋጅ 2 ቢሊዮን 247 ሚሊዮን 385 ሺህ 094.02 ብር ሆኖ የቀረበውን የምክርቤት አባላት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *