ኢቢሲ በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ትልቅ ተቋም ነው፡ – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

Spread the love

ኢቢሲ ኢትዮጵያን በመገንባት እና አንድነቷን በማጠናከር በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የራሱን አሻራ ያኖረ ትልቅ ተቋም ነው ሲሉ በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድ ካቲንግ ኮርፖሬሽን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ታርጫ ከተማ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ የሆነውን አዲስ ስቱዲዮ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ እንደ ኢቢሲ አይነት ዕድሜ ጠገብ ተቋማት ኢትዮጵያን በመገንነባት ሂደት ውስጥ ጠንካራ ሚና እንዳላቸው ፡፡

የኢትዮጵያ የተጋመደ ጉዞ መገለጫው የተቋማት ግንባታ ነው ያሉት ዶክተር ቢቂላ፤ እንደ ኢቢሲ ያሉ አንጋፋና ጉምቱ ተቋማት ኢትዮጵያውያንን እያጋመዱ፣ ወንድማማችነትን እያጠናከሩ፣ ቂምና ቁርሾን ሳይሆን ፍቅርን እየሰበኩ ለሀገር ግንባታ የራሳቸውን አሻራ አኑረው እዚህ ደርሰዋል ብለዋል፡፡

ኢቢሲ አንድነትን፣ አብሮነትን እንዲሁም የትስስር ታሪኮችን እየገነባ የመጣ ተቋም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ነው ዘንድሮ 25 60 90 በሚል የኤፍ ኤም አዲስ፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬዲዮን ምስረታ በተለያዩ መሰናዶዎች በማክበር ላይ የሚገኘው ብለዋል፡፡

‘ኢቢሲ ወደ ይዘት’ በሚል መሪ ቃል ተጨማሪ ይዘቶችን ለማመንጨት ወደ ህብረተሰቡ ወርዶ የህብረተሰቡን ባህል፣ ቋንቋ እንዲሁም ፍላጎት በሚገባ ለመረዳት በሚየያስችል ሁኔታ በመስራት በተግባር እያሳየ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *