ህዝቡን ብቃት በማስተባበር በፓርቲ መሪነት ትላልቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል ፦አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

‎በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረተሰቡን በብቃት በማስተባበር በፓርቲ መሪነት ትላልቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል ሲል የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

‎የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ፓርቲያችን ብልጽግና ትላልቅ ሀሳቦችን በማፍለቅና በማመንጨት ወደ ተግባር በመቀየር የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል።

‎በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ውጤታማ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስረዎችን በመስራት የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃማነት ማረጋገጥ በመቻሉ የፓርቲያችን ቅቡልነት የማሳደግ እንዲሁም ለሁለንተናዊ ብልፅግናን ጉዞ ስኬት መሰረት የሚጥል ስኬታማ ስራዎች ተከናውነዋል።

‎የፓርቲው ፕሮግራሞች፣ እሳቤዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ዕቅዶች በአግባቡ በህዝቡ ዘንድ በማስረጽና የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችንና የውይይት መድረኮችን በመፍጠር በርካታ ስኬታማ ስራዎች ተመዝግበዋሌ።

‎በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተናበበና የተቀናጀ የፖለቲካ ስራ በሚል መሪ ሀሳብ በርካታ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በዘርፉ መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።

‎በዚህም የህዝቡን ንቅናቄ በመፍጠር ፣በሰላም ፣በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።

‎ በአዎንታዊ ሰላም ግንባታ፣በመልካም አስተዳደር ፣የኑሮ ውድነትን ለማቅለል፣በስራ አጥነት ቅነሳ፣በመሠረተ ልማት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ላይ ትላልቅ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።

‎በ 2018 በጀት ዓመት “የሀሳብና የተግባር አንድነት ለላቀ ድልና ስኬት “የዘርፉ ቁልፍ መርህ በመሆኑ በትጋት ና በተናበበ መልኩ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

‎መድረኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች፣ የታዩ ክፍተቶች ብሎም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በጥልቀት የሚገመገሙበት እንደሆነ አብራርተዋል። የ2017 በጀት ዓመት የዘርፉ ማጠቃለያ ሪፖርት በዘርፉ ም/ኃላፊ በአቶ ዓለሙ ገብሬ እየቀረበ ይገኛል።

መረጃው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *