




በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረተሰቡን በብቃት በማስተባበር በፓርቲ መሪነት ትላልቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል ሲል የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ፓርቲያችን ብልጽግና ትላልቅ ሀሳቦችን በማፍለቅና በማመንጨት ወደ ተግባር በመቀየር የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ውጤታማ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስረዎችን በመስራት የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃማነት ማረጋገጥ በመቻሉ የፓርቲያችን ቅቡልነት የማሳደግ እንዲሁም ለሁለንተናዊ ብልፅግናን ጉዞ ስኬት መሰረት የሚጥል ስኬታማ ስራዎች ተከናውነዋል።
የፓርቲው ፕሮግራሞች፣ እሳቤዎች፣ ፖሊሲዎች፣ ዕቅዶች በአግባቡ በህዝቡ ዘንድ በማስረጽና የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችንና የውይይት መድረኮችን በመፍጠር በርካታ ስኬታማ ስራዎች ተመዝግበዋሌ።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተናበበና የተቀናጀ የፖለቲካ ስራ በሚል መሪ ሀሳብ በርካታ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በዘርፉ መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህም የህዝቡን ንቅናቄ በመፍጠር ፣በሰላም ፣በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።
በአዎንታዊ ሰላም ግንባታ፣በመልካም አስተዳደር ፣የኑሮ ውድነትን ለማቅለል፣በስራ አጥነት ቅነሳ፣በመሠረተ ልማት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ላይ ትላልቅ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።
በ 2018 በጀት ዓመት “የሀሳብና የተግባር አንድነት ለላቀ ድልና ስኬት “የዘርፉ ቁልፍ መርህ በመሆኑ በትጋት ና በተናበበ መልኩ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
መድረኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች፣ የታዩ ክፍተቶች ብሎም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በጥልቀት የሚገመገሙበት እንደሆነ አብራርተዋል። የ2017 በጀት ዓመት የዘርፉ ማጠቃለያ ሪፖርት በዘርፉ ም/ኃላፊ በአቶ ዓለሙ ገብሬ እየቀረበ ይገኛል።
መረጃው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ነው።
