ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ባመጣችው ለውጥ ፓኪስታን በዓለም መድረክ ስትራቴጂያዊ አጋሯ አድርጋ ትሰራለች፡- የሀገሪቱ ሴኔት መሪ ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ



ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ባመጣችው ለውጥ ፓኪስታን በዓለም መድረክ ስትራቴጂያዊ አጋሯ አድርጋ እንደምትሠራ የሀገሪቱ ሴኔት መሪ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ ገለጹ።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባሰናዳው መድረክ የፓኪስታን ሴኔት መሪ ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው ሥራ የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን በተፈጥሯዊ መንገድ መፍትሄ ያበጀ በመሆኑ ፓኪስታን በጋራ የትብብር ከፍታዋ አድርጋ ከኢትዮጵያ ጋር ትሠራለች።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በሀገር ውስጥ የተገኘውን የዘርፉን ውጤት ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ትግበራ እየተጠቀመችበት ስለመሆኑም አንስተዋል።
ኢትዮጵያና ፓኪስታን የጀመሩትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት በዓለም መድረክ የአየር ንብረት ለውጥ ፍትህ እንዲሰፍን ዓይነተኛ መታገያ ለማድረግ እየሰሩ ስለመሆኑም አክለው መናገራቸውን ኢቢሲ መረጃ ያመለክታል።
ባለፋት ሦስት ቀናት ከተለያዩ ክልላዊ መሥተዳደሮች የተውጣጣ የወጣቶች ልዑክ በፓኪስታን ከተሞች የኢትዮጵያን ተሞክሮ የማጋራትና የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሐ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
