የዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ-በኣ የአብሮነት፣የፍቅርና የታርክ መገለጫ እንደሆነ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ

Spread the love

የዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ-በኣ የአብሮነት፣የፍቅርና የታርክ መገለጫ እንደሆነ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ

የዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ-በኣ የአብሮነት፣የፍቅርና የታርክ መገለጫ እንደሆነ በዳውሮ ዞን ገሣ ጫሬ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል።

የሀገር ሽማግሌዎቹ ቶክ-በኣ በብሔረሰቡ ዘንድ ከጥንትም ጀምሮ የሚከበርና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል እንደሆነ ገልጸው የተጣለው የሚታረቅበት፣አሮጌ አመት የሚሸኝበት ፣ አዲሱ አመት የሚቀበልበት እና አዲሱ አመት የጥጋብ ፣የሰላም፣የፍቅርና የእርቅ እንዲሆን የሚጸለይበት በዓል መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ መሠለ ማራ ይባላሉ የሚኖሩት በገሣ ጫሬ ከተማ አስ/ር በጪጮ ቀበሌ ነው። በማህበራዊ ኑሮአቸው እጅግ ተወዳጅ፣ አስታራቅና ታሪክ አዋቅ ናቸው። አቶ መሠለ ስለ ዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ-በኣ በዓልም እንዲህ ስሉ ይናገራሉ:- የቶኪ በኣ በዓል ከጥንትም ጀምሮ በዳውሮ ብሔረሰብ ዘንድ በልዩ ሁኔታ እየተከበረ የቆየና የመጣ ነው ይላሉ።

የቶኪ-በኣ በዓል ስደርስ የተለያዩ ባህላዊ ምግብና መጠጥ ይዘጋጃል፣ጎረቤቶች ተሰብስበው በሰፊው መዳ ይበላሉ ይጠጣሉ ፣የተጣሉት ይታረቃሉ ፣ምስትና ባል ተፋቶ የቆዩ ቢሆኑ እንኳ በዛን ቀን ይታረቃሉ በቤታቸው በዓሉን ያከብራሉ ስሉም ይናገራሉ።

ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ደጀኔ ባቡሎ ይባላሉ የሚኖሩት በገሣ ጫሬ ከተማ አስ/ር በከተማ ቀበሌ ነው። አቶ ደጀኔ ሰው አክባሪ ፣ ታርክ አስተማር፣ የተጣላን አስታራቂና መካሪ አባት ናቸው። አቶ ደጀኔ በቶኪ-በኣ በዓል ዕለት ከቤት እንስሳት እስከ ሰው ጠግቦ ይበላል ፣ልጆች ይቦርቃሉ ፣ሳር ቅጠሉ ይለመልማል ስሉም ይናገራሉ።

አቶ ደጀኔ ጨምሮም በበዓሉ ዕለት የቤት መገልገያ ቁሳቁስ ሙሉ ለሙሉ ሞልቶ ያድራል። ጎዶሎ ሆኖ ካደረ ቶኪ-በኣ ቶኪ በኤ(መዝኖ) ያያል ተብሎ ስለሚታሰብ ይላሉ።

አቶ ገ/ማሪያም ዋተሻ ይባላሉ የሚኖሩት በገሣ ጫሬ ከተማ አስ/ር በቦሳ ቀበሌ ነው። እኝህ አባት ስለ ቶኪ-በኣ በዓል እንዲህ ስሉም ይናገራሉ :- ቶኪ-በኣ የተጣላን የሚያስታርቅና ለሰዎች ሠላምን የሚያውጁ ፣ ጥጋብንና አዲስ ተስፋን ይዞ የሚመጣ በዓል ነው ቶኪ-በኣ ይላሉ።

ሌላኛው የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ አሰፋ አሳሮ ይባላሉ የሚኖሩት በገሣ ጫሬ ከተማ አስ/ር በጫሬ ቀበሌ ነው። እሳቸው እንደሚናገሩት ከሆነ ቶኪ-በኣ ትውልድ ተሻጋሪ በዓል እንደሆነም ይገልፃሉ።

አቶ አሰፋ የአሁኑ ትውልድ የቶኪ-በኣ በዓልን ከመቸውም ጊዜ በላይ በየአመቱ ከመላው ብሔረሰብ ጋር በጋራ በመሆን እያከበረ ይገኛል ።ይህም የብሔረሰቡን ወግ፣ታርክ፣እሴት ቅርስን ለመላው አለም አጉልቶ የሚያሳይበት መንገድ ነው ይህም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ስሉ በሰፊው ያወሳሉ።

ዘመን መለወጫ (ቶኪ-በኣ) ዋዜማ ስደርስ አባወራዎች የበሬ ፣የበግ፣የፍየልና የዶሮ ስጋ ዝግጅት ከጎረቤት ጋር ያዘገጃጃል። እማወራዎች ደግሞ የቅመማ ቅመም ፣የቅቤ፣የአይብ ፣የኦጭኖ(ቦይያ) ፣የጎደሬ(ቦይና) ፣ የቦርዴ መጠጥና የሌሎችም ዝግጅት ያሰናዳሉ። ልጆች የበዓሉ ጊዜ መጥቶ መጫወትንና መደሰትን አቋርጦ ለስራ ላለመሄድ ስሉ በዓሉ ሳይመጣ በፊት የማገዶ እንጨት ፣የከብቶች ሣር ፣ እና ሌሎችንም የቅድመ ስራዎችን አስተካክሎ ይጠብቃሉ።

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ለዳውሮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ቶክ-በኣ በዓል!

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *