ክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ ውይይት መድረክ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።



በዚሁ የጋራ ውይይት ላይ የተገኙትየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ በወቅቱ እንደገለፁት ምክር ቤቱ ህገ መንግስት በሰጠው ስልጣን መሠረት መመሪያዎችን እንዲሁም ህግን በተከተለ አግባብ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።
በዚህም ምክር ቤቱና ቋሚ ኮሚቴዎች የየራሳቸውን እቅድ በማዘጋጀት ተግባራትን በተደራጀ መንገድ እንዲመሩ ለማስቻል የተዘጋጀ የጋራ ውይይት መሆኑን ዋና አፌ ጉባኤው ተናግረዋል ።
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት የ2018 የህግ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ዕቅድ ፣ የበጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዕቅድና የ2018 መነሻ ዕቅዶች ዙርያ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች ውይይት በማድረግ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጡ ተገልጿል ።
በጋራ ውይይቱ ላይ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ዋና አቶ መቱ አኩ ፣ ምክትል አፌ ጉባኤ አቶ መሰለ ከበደን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ሸካ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
