መንግስት የመኖሪያ ቤት ችግርን ለማቃለል ከግል አልሚዎች ጋር የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ ይቀጥላል
መንግስት የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለማቃለል ከግል አልሚዎች ጋር የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

‘ሀቢታት ፎር ሂዩማኒቲ’ በኢትዮጵያ በመኖሪያ ቤት አቅርቦት ረገድ እያከናወነ ባለው ተግባር ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ውይይት አካሒዷል።
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ በውይይቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት መንግስት የዜጎችን የቤት አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ለዚህም የአገራትን ልምድና ተሞክሮ መቅሰም፣በዘርፉ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ማድረግና በጥናት ላይ የተመሰረተ የቤት ልማት አማራጮችን ተግባራዊ ማድረግም እንዲሁ።
በተለይም በቤት ልማት ከተሰማሩ የግል አልሚዎች ጋር በመተባበር የሚከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ናቸው ነው ያሉት።
ከ’ሀቢታት ፎር ሒዩማኒቲ’ ጋር የተደረገው ምክክርም እነዚህን ስራዎች ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዝ እንደሆነ ሚኒስትር ዴኤታዋ አብራርተዋል።
መንግስት ከግል አልሚዎች ጋር በመተባበር የሚያቀርበውን የቤት አቅርቦት ለማስፋት በቁርጠኝነት እየሰራ ስለመሆኑም ሚኒስትር ደኤታዋ አረጋግጠዋል።
የ’ሀቢታት ፎር ሒዩማኒቲ’ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆናታን ሮክፎርድ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች የቤት አቅርቦትን ተደራሽ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በቤት ልማት ዘርፍ የምታካሄዳቸው ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልፀው፤ የተዘጋጁ አማራጮች ተደራሽነቱን ለማስፋት አይነተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።
የ’ሀቢታት ፎር ሒዩማኒቲ’ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ይጥናው ተካልኝ እንደገለጹት መንግስት በቤት ልማት ዘርፍ እያከናወነ ያለው ተግባር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማጎልበት እድል ፈጥሯል።
ውይይቱ በዘርፉ ያሉ ስኬቶችን በጋራ ለማስቀጠል ብሎም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።
በመሆኑም በቀጣይ በበጎ ፍቃድ በሚሰሩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች ላይ በስፋት ለመሳተፍ ድርጅቱ ፍላጎት እንዳለው ጠቁመው፤ ለዚህም የተደረገው ምክክር በእጅጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
