የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት ያካሂዳል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በነገው ዕለት በቴፒ ከተማ ያካሂዳል።

ጉባኤውን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ በጉባኤው የምክርቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል ።
ከዚህም በተጨማሪ የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ የሚገመገም ሲሆን ልዩ ልዩ አጀንዳዎችም ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸው ይፀድቃሉ ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል ዋና አፈጉባኤው።
ለጉባኤው ስኬት አስፈላጊው ቅደመ ዝግጅት መጠናቀቁን የገለፁት ዋና አፌ ጉባኤው በዕለቱ የምክር ቤቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሰዓቱ እንዲገኙም ጥሪ አስተላልፈዋል ።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
