የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት አገልግሎትን ውጤታማነት ያሳድጋል – ምሁን
የደመወዝ ማሻሻያው ቀልጣፋ እና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት መስጠት ያስችላል አሉ የምጣኔ ሃብት ምሁራን፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
መንግስት የኑሮ ውድነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የመንግስት ሠራተኞችን የኢኮኖሚ ሁኔታ በማጤን የሰጠው ምላሽ የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ማሻሻያው ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታልም ነው ያሉት፡፡
የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የደመወዝ ማሻሻያው ሠራተኞች ከብልሹ አሰራር በመራቅ ሥራቸውን ጠንቅቀው እንዲከውኑ ያስችላል ብለዋል፡፡
የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማሻሻያ ትግበራ ሒደት ላይ ውጤትን መሠረት ያደረጉ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቁመዋል።
በዘላቂነት በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል መንግስት በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ምሁራኑ አስገንዝበዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
