የኢትዮጵያ ልማት ለአፍሪካ ተምሳሌት ለጎረቤት ሀገራት ብልጽግና የሚሆን ነው፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Spread the love

የኢትዮጵያ ልማት ለአፍሪካ ተምሳሌት ለጎረቤት ሀገራት ብልጽግና የሚሆን ነው፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የኢትዮጵያ የልማት ሥራ ለአፍሪካ ተምሳሌት ለጎረቤት ሀገራት ዕድገትና ብልጽግና የሚሆን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በድሬዳዋ ያደረጉትን ቆይታ አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በድሬዳዋ ከተማ የተሰሩትን የኮሪደር ልማትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን አድንቀዋል፡፡

የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ ንግድና ኢንቨስትመንትን በማሳለጥ ከነዋሪዎች አልፎ ለጎረቤት ሀገራት ምቹና ተስማሚ ከባቢ መፍጠር የሚያስችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በድሬዳዋ ለነዋሪዎች ጥያቄ ምላሽ የሰጡና ትውልድ የሚቀርጹ ቤተ-መጽሐፍትና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከተማዋ የጥንታዊነቷን ያክል ትኩረት ሳይሰጣት መቆየቱን ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግስት የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ጠንካራ ትስስር እንዳላት የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የጎረቤት ሀገራት ሚኒስትሮች ድሬዳዋን በመጎብኘት በልማት የመሳተፍ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ልማትና ዕድገት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገራት ብልጽግና ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎች በአፍሪካ ተምሳሌት እንዲሆኑ የተጀመረው ጥረት ፍሬ እያፈራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዋነኛ ጠላት ድህነት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፤ ድህነትን ለማሸነፍ ሰላምና ጸጥታ ከልማት ጥያቄ ጋር መመለስ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለውን የልማት ውጤት ተከትሎ የሰላም ሁኔታው እየተሻሻለ መሆኑን ጠቁመው፤ ባለሀብቱና ህዝቡ የልማቱ ተዋናይ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖን በዘላቂነት ለመከላከል በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ላይ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 

👇
📌

በትዊተር twitter.com/sweprs

📌

በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *