የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሻግዳን ኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን ፕሮጀክት ጉበኙ

Spread the love

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሻግዳን ኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን ፕሮጀክት ጉበኙ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በኦሞ ቁጥር-3 ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገነባውን የሻግዳን ኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ጉብኝት አድርገዋል።

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ እሸቱ ገ/ማርያም የምርጫ ክልላቸው የሆነውን የማጂ ወረዳ እና አካባቢውን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለውን የሻግዳን የኤሌክትሪክ ሳብስቴሽን ግንባታን ነው የጎበኙት።

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የማጂ ወረዳ ህዝብ በመራጭ ተመራጭ ውይይት ላቀረበው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ጥያቄ መንግስት ምላሽ ለመስጠት በዕቅድ የያዘ መሆኑን የተከበሩ አቶ እሸቱ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸጋዳን የኤሌክትሪክ አቅርቦት የፈታል በሚል ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሰጠውን ምላሽ አስመልክቶ በምላሹ መሠረት መሬት ላይ ያለውን አፈፃፀም ለማረጋገጥ የተከበሩ አቶ እሸቱ ገ/ማርያም የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በአካባቢው ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋን የሌለበት በመሆኑ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ህዝቡ በኤሌክትሪክ ዙሪያ ለሚያነሳው የፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተከበሩ አቶ እሸቱ አስገንዝበዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በማጂ እና በሰላማጎ ወረዳዎች መካከል አዋሳኝ ቦታ የሚገነባው የሻግዳን የኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን የግንባታው አፈጻጸም በተሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ኦሞ ቁጥር-3 እና ለሌሎች የስኳር ፋብሪካዎች አገልግሎት የሚሰጥ እንዲሁም ኦሞ ወንዝን ተከትሎ ለሚከናወኑ የግብርና ኢንቨስትመንት ስራዎች ብሎም ለሁለቱ ክልል አዋሳኝ ህዝቦች አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ኃላፊ ኢንጀነር መኮንን ጥላሁን እንደገለፁት ከኮሪያ እና ከኤግዚም ባንክ በተገኘ 28 ሚሊዮን ዶላር እየተገነባ የሚገኝ ፕሮጀክት እንደሆነ አብራርተዋል።

ጥር/2016 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው የሻግዳን ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 230 KvA ያመነጫል ያሉት ኢንጅነር መኮንን አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም አጠቃላይ 60 በመቶ ላይ እንደሚገኝ እና የፕሮጀክቱ ስራ በ2018 በጀት ዓመት ህዳር ወር እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ እሸቱ ገ/ማሪያም የህዝቡን የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ጥያቄ ለመመለስ በፌደራል መንግስት የተወሰደው ቁርጠኝነት አበረታች መሆኑን ገልፀው፤ የግንባታው አፈፃፀም እየተፋጠነ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተደረገ ያለው ጥረት ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት የተከበሩ አቶ እሸቱ፤ህዝቡ በጉጉት የሚጠብቀው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በመሆኑ ፕሮጀክቱ ግንባታው በተቀመጠለት ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቅ ማሳሰባቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *