ለመንግስት ሠራተኛው የደመወዝ መጨመርን ተከትሎ ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይከሰት የመከላከል ተግባር ቅድሚያ ተሰጥቶት ይከናወናል

Spread the love

ለመንግስት ሠራተኛው የደመወዝ መጨመርን ተከትሎ ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይከሰት የመከላከል ተግባር ቅድሚያ ተሰጥቶት ይከናወናል።አቶ ተመስገን ከበደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በቂ ምርት በማቅረብ ዋጋን ለማረጋጋት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ሕገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት ለመከላከልም ግብረ ኃይል መቋቋሙን ቢሮው ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በክልሉ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በቂ ምርት በማቅረብ ዋጋን ለማረጋጋት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለመንግስት ሠራተኛው የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ እንዳይከሰት የመከላከል ተግባር ቅድሚያ ተሰጥቶት እንደሚከናወንም የቢሮ ሀላፊው አስታውቀዋል።

ለዚህም በክልሉ ሁሉም መዋቅሮች ግብረ ኃይል መቋቋሙን እንዲሁም የምርት እጥረት እንዳያጋጥምና ያልተገባ ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ይድረጋል ብልዋል።

ነዳጅ ላይ በልዩነት ቁጥጥር ይድረጋል ያሉት ቢሮ ኃላፊው፣ ለሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ ከአምና ጀምሮ እየተሰራበት ያለው አዋጅ መጣስ እንደሌለበትም አሳስበዋል።

በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ለሸማቹ በቂ ምርት በማቅረብ ዋጋን ለማረጋጋት የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማመልከታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

ኅብረተሰቡ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሲያጋጥመው ለቢሮው ፈጥኖ ጥቆማ በማድረስ መብቱን እንዲያስጠብቅም ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *