ምክር ቤቱ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን መቻሉን የብሔረሰቦች ምክርቤት አባላት ተናገሩ ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በቀረበው የ2017 በጀት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ አባላት መክረውበታል።




የምክርቤት አባላት በበጀት ዓመቱ የሚበረታቱና የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል ።
በክልሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ግጭቶች በዘላቂነት የሚፈቱበት ሁኔታ እንዲጠናከር ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን እንዲሁም አብሮነትን የሚያዳብሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊሰሩባቸው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል ።
የሱሪና ዚልማሞ ብሔረሰብ ቋንቋ ልማት ፣ እና የሰላም እሴት ግንባታዎች ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የምክር ቤት አባላት አስተያየት ሰጥተዋል።
የመሠረተ ልማት ውስንነት ያለባቸውን አካባቢያዎች በጥናት በመለየት በክልሉ መንግስት በኩል ልዩ ድጋፍ በመስጠት ተመጣጣኝ ልማት እንዲረጋገጥ በምክር ቤት በኩል በትኩረት እንዲሰራ የምክርቤት አባላት ጠይቀዋል።
የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ስርዓት መሻሻሎች ያሉበት ቢሆንም የቅሬታና አቤቱታ አፈታት ሁኔታ ያለበት ደረጃ በተገቢው ሊገመገም ይገባልም ሲሉ ጠይቀዋል።
የሰላም እሴት ግንባታና ግጭት አፈታት ሂደቱ ዘለቂ እንዲሆንም ሀገር በቀል ግጭት አፈታት ዘዴዎች ተቋማዊ ሆነው ሊቀጥሉ ይገባልም ብለዋል።
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ በቀረቡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በክልሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ግጭቶች በሀገር በቀል ግጭት አፈታት ዘዴዎች እየተፈቱ መሆኑን ያብራሩት ዋና አፈጉባኤው ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የማጠናከር ስራዎች ተጠናክረው ይሰራሉ ብለዋል።
የህዝቦች ወንድማማችነትና እህትማማችነት ይበልጥ እንዲጎለብት ችግሮችን በጋራ መፍታት ከሁሉም የሚጠበቅ ሀላፊነት መሆኑንም በምላሻቸው አብራርተዋል።
ከዩኒቨሲቲዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ በማጠነከርም በቋንቋና ባህል ልማት ላይ ይበልጥ ይሰራል ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በምክርቤቱ ጉባኤ ላይ በመገኘት ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።
በህብረተሰቡ አካባቢ የሚፈጠሩ ቅሬታዎች እንዳይባባሱ ወደ ህብረተሰቡ በመቅረብና በማዳመጥ ችግሮችን የመፍታት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም ተናግረዋል ።
ግጭት ቀስቃሽ አካላትን የመለየትና የህግ የበላይነት ማረጋገጥ : ግጭቶች ሲከሰቱም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ በመቀናጀት መፍታት እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።
ከነባሩ ደቡብ ክልል የነበረ የጋራ ሀብት ክፍፍልን በተመለከተም ለተነሳው የሀብት ክፍፍል በማድረግ የክልሉን ድርሻ መውሰድ መቻሉን እና ቀሪ ቋሚ ንብረቶች ክፍፍል የተጠናቀቀ ቢሆንም ወደ ሃብት የመቀየሩ ሂደት ከሌሎች ሶስት ክልሎች ጋር በምክክር ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን ህዝብ በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ሊሰሩባቸው ይገባልም ብለዋል።
በብሔረሰቦች ምክርቤት የዛሬው ውሎ ከምክርቤት አባላት ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተጨማሪ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት 4ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በቀረበው የ2017 በጀት አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2018 ጠቋሚ ዕቅድ ከተወያዩ በኋላ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
በታጠቅ አበበ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
