ዲጂታል ኢትዮጵያ የገበያ ትስስር በመፍጠርና ያልተገባ ወጪን በማስቀረት ለንግዱ ማህበረሰብ የተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረገ ነው

Spread the love

ዲጂታል ኢትዮጵያ የገበያ ትስስር በመፍጠርና ያልተገባ ወጪን በማስቀረት ለንግዱ ማህበረሰብ የተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረገ ነው

ዲጂታል ኢትዮጵያ በገበያ ትስስር፣በጊዜ ቁጠባና ያልተገባ ወጪን በማስቀረት ለንግዱ ማህበረሰብ የተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ገለጸ።

ለመንግስት ሠራተኛው የደመወዝ ማሻሻያ መደረጉ በገበያ ላይ ምንም አይነት ችግር እንደማያመጣም ተገልጿል።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሰብስብ አባፊራ÷የንግድ ምክር ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት መወጣት የሚያስችል ስትራቴጂክ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል።

የንግዱ ማህበረሰብም በሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚያስችል ዝግጅት የሚያደርግበትን የማንቃትና የማዘጋጀት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራና ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት የንግዱን ማህበረሰብ የሚያዘጋጁ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክክር መድረኮች መፈጠራቸውን አንስተዋል።

መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚያደርገው ጥረትም ምክር ቤቱ የንግዱን ማህበረሰብ አገልግሎቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲጠቀም እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ ሥርዓትም በገበያ ትስስር፣በጊዜ ቁጠባና ያልተገባ ወጪን በማስቀረት ለንግዱ ማህበረሰብ የተሳለጠ የመንግስት አገልግሎት እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የንግድ ጤናማነትና የሕግ ተከባሪነት ሥርዓትን ለማስቀጠልም ከፌደራል እስከ ወረዳ ከሚገኙ ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት በተፈጠረበት ወቅት ለመንግስት ሠራተኛው የደመወዝ ማሻሻያ መደረጉም በገበያ ላይ ምንም አይነት ችግር አይመጣም ብለዋል።

የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ስኬታማ ተግባራትም በግብይት ምርት አቅርቦትና ፍላጎት ላይ አዎንታዊ ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል።

የመንግስት ሠራተኛን የደመወዝ ማሻሻያ ሰበብ በማድረግ በግብይት ወቅት ኢ-ምክንያታዊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረጋል ብለዋል።

የመንግስት ሠራተኛው የደመዝ ማሻሻያም በግብይት ሥርዓቱ ላይ ምንም አይነት ክፍተት የሚፈጥርበት ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል።

የንግዱ ማህበረሰብም ከምንጊዜም በላይ ሸማቹን ህዝባቸውን በተገቢው ሁኔታ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅበት መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *