የፅናት ቀን በፀጥታ እና ደኅንነት መስኮች ለተመዘገቡ ሁለንተናዊ ስኬቶች ዋጋ የምንሰጥበት ነው – የመከላከያ ሚኒስቴር


ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም “ፅኑ መሠረት ብርቱ ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ የፅናት ቀን በሚል ተሰይሞ እንደሚከበር የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገልጸዋል።
ቀኑን ትርጉም ባለው መልኩ ለማክበር የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸው ተመላክቷል።
ነገ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በሚከበረው በዓል የተለያዩ የጥበብ ሥራዎች እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።
በበዓሉ ላይ ኢትዮጵያ የፀጥታ እና ደኅንነት ተቋሞችን ለማዘመን የሄደችበት ጉዞ እና የተመዘገቡ አስደናቂ ስኬቶች የፅናታችን መገለጫ ሆነው ይቀርባሉ ብለዋል ሚኒስትሯ።
ቀኑ በፀጥታ እና ደኅንነት መስኮች ላስመዘገብናቸው ሁለንተናዊ ስኬቶች ዋጋ የምንሰጥበት፣ ለቀጣይ በፅናት መቆማችንን የምናሳውቅበት እና ሀገራችንን ወደ ላቀ የብልፅግና ከፍታ ለማድረስ የሚያስችለንን የፅናት መንፈስ የምናድስበት ነው ብለዋል።
ዕለቱ የሚከበረው በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ዋዜማ ላይ በመሆኑ ደስታችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል ብለዋል ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገር ምልክት፣ የሕዝባችን ፅናት ማሳያ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ግድቡ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የብልፅግና ጉዞ ለማሻገር ያለው አቅም የላቀ በመሆኑ ኩራት ይሰማናልም ብለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
