በአየር ንብረት ለውጥ አማካኝነት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለመቋቋም ወጣቶች በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል
በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ አማካኝነት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለመቋቋም ወጣቶች በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ቅኝት በትብብር መስራት እንደሚጠበቅባቸው የፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ሚቲካ ምወንዳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡



ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ስብሰባ ቅድመ ጉባኤ አካል የሆነው የአፍሪካ ወጣቶች የአየር ንብረት ስብሰባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመርሀ-ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ወጣቶችም እየተሳተፉ ነው፡፡
የፓን አፍሪካ የአየር ንብረት ፍትህ ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ሚቲካ ምወንዳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ዋጋ የምትከፍለው ሌሎች በፈጠሩት ችግር ነው፡፡
በአፍሪካ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ2025 ብቻ ከ110 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በጎርፍ በድርቅና በሌሎች የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰቱ አደጋዎች የጉዳት ሰለባ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የአህጉሪቷ የሙቀት መጠን በመጨመር ዜጎች በተለያዩ ችግሮች ወደ ሌሎች ክፍለ አህጉራት እንዲሰደዱ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ እነዚህን ፈተናዎች የምታስተናግደው ባልፈጠረችው የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መሆኑን ገልጸው፤ ይሄውም የዓለም የአየር ንብረት ፋይናንስን ኢ ፍትሐዊነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ወጣቶች አቅማቸውን አስተባበርው በጋራ ካልቆሙ አደጋው ይቀጥላል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ቅኝት በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ወጣቶች የአየር ንብረት ስብሰባ አህጉራዊ አጀንዳ ለመቅረጽ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት መድረኩን ለማዘጋጀት ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሱፍ መሀመድ ዑስማን በበኩሉ፤ የአየር ንብረት ለውጥ በአፍሪካ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ከዚህ በላይ መራዘም የለበትም ብሏል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ የዜጎችን ህይወት እየረበሸ መቀጠል የለበትም ያለው ወጣት የሱፍ፤ የተራዘመ ድርቅና ጎርፍ የሚፈጥረውን አደጋ በጋራ መመከት እንደሚገባም ገልጿል፡፡
የዚህ ዘመን ወጣቶች በአረንጓዴ አሻራ እና በታዳኝ ሀይል ልማት የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ትግል እያደረገ መሆኑን ተናግሯል፡፡
የአፍሪካ ወጣቶች የአየር ንብረት ስብሰባ በድርቅ፣ ጎርፍና አውሎ ነፋስ ለምትጠቃው አፍሪካ የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማመንጨት ያግዟል ብሏል ያለው ኢዜአ ነው፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
