ነፃና ገለልተኛ የሲቭል ሰርቪስ ግንባታን ማፋጠን እንዲሁም ብዝሃነት እና አካታችነትን ያረጋገጠ የጤና ሴክተር ሰራተኞች ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

Spread the love

ነፃና ገለልተኛ የሲቭል ሰርቪስ ግንባታን ማፋጠን እንዲሁም ብዝሃነት እና አካታችነትን ያረጋገጠ የጤና ሴክተር ሰራተኞች ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

‎የክልሉ ጤና ቢሮ አመራርና ባለሙያዎች በተገኙበት የጤና ሴክተር የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ትግበራ ጽንሰ ሀሳብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት መድረክ ተካህዷል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት ብዝሃነት እና አካታችነትን ያረጋገጠ የጤና ሴክተር ሰራተኞች ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል።

‎በአገር ደረጃ ለሪፎርሙ ትግበራ ከተመረጡት አራት ቢሮዎች ውስጥ ጤና ቢሮ አንዱ መሆኑን የገለጹት አቶ ኢብራሂም ሪፎርሙ ሲተገበር ግልጽና ተጠያቅነት ስርዓትን በመዘርጋት ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የጤና ሴክተር የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም አምዶች ስር የሚከናወኑ ተግባራት፣ ቀጣይ አቅጣጫ እና በዞንና ወረዳ የሚጠበቁ የሪፎርም ተግባራት፣ በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉዳዮችና መፍትሔዎች እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ውይይት ተደርጎባቸዋል።

‎በሪፎርሙ የጤናው ሴክተር ገቢር ነበብ አመራር እና ተቋም ግንባታን ማፋጠን በትኩረት እንደሚሰራና ዲጂታላይዜሽንና ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥን ማዕከል ማድረጉ በውይይቱ ተነስቷል።

‎የጤና ልማትና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዋሲሁን ዓለማየሁ የውይይት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ባቀረቡት ሰነድ ላይ ሪፎርሙ በሲቪል ሰርቪስ የሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለመፍታት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሻሻል፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ፣ የዘመነ ፣ ወጭ ቆጣቢ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነ የሰው ሀይል መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል።

‎ በቀጣይ የሪፎርሙ ትግበራ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በዞኖች፣ በከተማ አስተዳደሮች እና በወረዳዎች ለሚገኙ ጤና ባለሙያዎች እና አመራሮች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የቢሮው ሀላፊ ከየስራ ዘርፍ ሀላፊዎች ጋር የቢኤስ ሲ የውል ሰነድ ተፈራርመዋል ሲል ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *