የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
የጽናት ቀን
ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር
ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው፡፡ በሁሉም ዘርፎች በምናደርገው ተጋድሎ የኢትዮጵያን መሠረት እናጸናለን፡፡ ለማናቸውም ችግሮች የማትበገር፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የምትቀይር፣ በመጪው ዘመንም ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን፡፡