ከአየር ንብረት ርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ ይገባል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሔውም አህጉር መሆኗን በአፅንዖት ተናግረዋል።



እንደ አረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ የተመቸ ግብርና እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማንሳት የኢትዮጵያን ሥራዎች በምሳሌነት አውስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአየር ንብረት ርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸው፤ “ክላይሜት ኢኖቬሽን ኮምፓክት” የተሠኘ በ2030 አንድ ሺህ አፍሪካ መር መፍትሔዎች የሚገኙበትን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።
አፍሪካ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና የሥነ ምኅዳር ጥበቃ የመምራት አቅሟንም አንስተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአውሮፓውያን 2027 የኮፕ 32 ጉባዔን ለማስተናገድ ያላትን ጥያቄም ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም ኢትዮጵያን እና አፍሪካን በአየር ንብረት ጥበቃ ተግባር የመሪነት ሚና የሚያጎናፅፍ ይሆናል ማለታቸዉን ኢቢሲ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
