“ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የራስን መቻል ምልክት ለኢትዮጵያ ደግሞ አዲስ ምዕራፍ ነው” – የኬንያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት

Spread the love

“ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የራስን መቻል ምልክት ለኢትዮጵያ ደግሞ አዲስ ምዕራፍ ነው” – የኬንያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት

ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም የገነቡት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የራስን መቻል ምልክት ለኢትዮጵያ ደግሞ አዲስ ምዕራፍ መሆኑን ኬንያ አስታውቃለች።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ምረቃ መርሐ ግብር ላይ እንደሚገኙ የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በሚያገናኛት የኃይል ማስተላለፊያ መሰረት ልማት፤ አከባቢን የማይበክል ኃይል ከኢትዮጵያ በመተጣጣኝ ዋጋ እያገኘች መሆኑንም ነው ጽ/ቤት ያስታወቀው።

የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምታስገባውን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማጠናከር፤ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖራት ያግዛል ብሏል የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት በመግለጫው።

የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ ወደ ሥራ መግባት በኬንያ የአምራች ዘርፍ ዕድገት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳሚኖረውም ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያን ከኬንያ፣ ኬንያን ደግሞ ከታንዛኒያ ጋር የሚያገናኘው የኃይል ማስተላለፊያ መሰረተ ልማት፤ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ቀጠናዊ ትስስርና የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚያበረክትም ጠቁሟል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

#EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *