በቀጣይ ከምርታማነት በላይ እይታ ለሀገር ገፅታ እና ለኤክስፖርት እምርታ የሚንዘጋጅበት ጊዜ ሊሆን ይገባል ተባለ
ጳጉሜን 3 ቀን “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በቦንጋ ከተማ ተከብሯል።




ብልጽግና ሀገራዊ ፓርቲ ሆኖ ከተመሠረተ ወድህ የፖለቲካ ልምምዶችን ሊቀይር በሚችል መልኩ የኢትዮጵያ ልዩ ቀመር በሆነው ጳጉሜ ቀናት በሽግግር መልኩ ልዩ ትርጓሜ በመስጠት እያከበረ መምጣቱ ይታወሳል።
ዘንድሮም በተመሳሳይ ሁኔታ እያንዳንዱ የጳጉሜን ቀናት ምክንያታዊ የሆኑ ስያሜዎችን ማግኘታቸውንና ጳጉሜን ሶስትም የእመርታ ቀን በሚል ሲሰየም “እምርታ” ትናንት የነበሩንን ጉድለቶች አርመን በቀጣይ ወደ ተምሳሌታዊ ሀገር የሚናመራበትን ጉዞ ለመጠቆም ያለመ መሆኑ ተገልጿል ።
አከባበሩን በንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ በሀገራችን የፖለቲካና አስተዳደር ታሪክ በለውጡ መንግስት ዘርፈ ብዙ እጥፋት የተመዘገበበት መሆኑን አውስተው በዝህም በወል ትርክት እሳቤ ብሐለራዊነትና አንድነት እንዲጎላ ከማድረጉም በላይ በአካታችነቱ ተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን ወደ ህዝብ ኃላፊነት አምጥተዋል ብለዋል።
የዕለቱ ትኩረት በሆነው ኢኮኖሚ ዘርፍ መዋቅራዊ ሽግግሮችን በመተግበር ዘርፎችን አሰባጥሮ በግርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በቴክኖሎጂ ወደ ስራ የገባው መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚጨበጥ ውጤት ማስመዝገቡ ተገልፀዋል።
በግብርና ዘርፍ የለውጡ መንግስት ትሩፋት የሆነው ክልላችን ያለውን እምቅ አቅም ወደ ምርት ለመቀየር በተንቀሳቀሰባቸው ሁሉም ዘርፎች ከተለያዩ ኢኒሼቲቮች ጋር በማጣመር በሌማት ትሩት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በቡናና ቅመማቅመም፣ በአጠቃላይ እርሻና እርባታ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡንም አብራርተዋል።
ግብርናችን ከምርታማነት በላይ እይታ ለሀገር ገፅታ እና ለኤክስፖርት እምርታ በሚደርስበት ሁኔታ ላይ በተሰራው ስራ ከዝህ በፊት በዙም በማይታሰቡ እንደ አፋር እና ሶማሊያ ክልሎች በቴክኖሎጂ የታገዘ መስኖና ኩታ ገጠም እርሻ የስንዴ ምርትን እስከ ኤክስፖርት ድረስ ማስፋፋት መቻሉም ተገልጿል።
በሀገራችን እየተመዘገቡ ያሉ እምርታዎችን ወደ ተሟላ ገፅታ ለመቀየር የሁሉም ጥረት አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ: የለውጡ መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ በወሰዳቸው እርምጃዎች ኢትዮጵያን ከነበረባት ዘርፈ ብዙ አረንቋ አወጥቶ የአፍሪካ ኃይል ሚዛን እያደረጋት ይገኛል ብሏል።
የዛሬን ዕለት በልዩ ትርጉም የሚናከብረው የመጣንበትን መንገድ በመፈተሽ በቀጣይ ሀገራችን ወደ ላቀ እምርታ እንዲትጓዝ ነው ያሉት አቶ አጥናፉ: ተምሳሌታዊ ሀገር እንዲትሆን ሁሉም በተሰማራበት መስክ እንዲተጋ በአጽንኦት አሳስበዋል።
መንግስት አረንጓዴ አሻራን አሳክተው ለሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ከመቀመር በተጨማሪ ለንግግር እንኳን የማይፈቀደውን የወደብ ባለቤትነት አጀንዳ ወደ ፊት ለ ፊት ማምጣት መቻሉ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ወቅት ላይ መሆኑ ለሁለንተናዊ ለእምርታ ማስፈንጠሪያ እንደሆነ ተመላክቷል።
ክልላዊ የኢኮኖሚ ዘርፍ ዋና ዋና እምርታዎችን በሰነድ ያቀረቡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አማካሪና ግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የሐንስ መላኩ ክልላችን ከተመሠረት ወድህ በካፕታል ፕሮጀክቶች፣ በማዕድን ዘርፍ፣ በግብርና፣ በእንቨስትመንትና ገቢዎች እንቅስቃሴ የተሰሩ ስራዎችን አሳይተው በቀጣይ ዓመታት ሊተገበሩ ወደ ታሰቡ ግቦች የሚያመራውን ጠቋሚ ነጥቦች አብራርተዋል።
በመጨረሻም በቀረቡት ነጥቦች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱት ሀሳብ እና አስተያየት ማብራሪያ ተሰጥተውበት በቀጣይ ወደ ተሟላ እምርታ በሚያመሩበት ጉዳዮች ላይ በመግባባት የጰጉሜ 3 ቀን አከባበር ተጠናቋል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
